1
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:9
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በትክክለኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:12
እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤
3
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:11
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ስለ ጠየቅህ፥
4
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:13
ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።
5
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:14
አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድና ለእኔ ብትታዘዝ፥ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።”
6
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:5
በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው።
7
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:7
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
8
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:10
ሰሎሞን ይህን በመጠየቁ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤
9
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:6
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት ደግ፥ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን ስታሳየው ኖረሃል፤ ዛሬም በእርሱ እግር ተተክቶ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል፥
10
አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 3:8
እነሆ እኔ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ሕዝብ መካከል እገኛለሁ፤
Home
Bible
Plans
Videos