ከ 1 ጴጥሮስ 5:6ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች

1ኛ ጴጥሮስ: የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድ
5 ቀናት
ተስፋ ተኮር በሆነው ደብዳቤው ለመጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ጴጥሮስ በማመን፣ በመታዘዝ እና ፍርድና መከራ ሲገጥመን ፀንተን እንድንቆም ያበረታናል፡፡ ይህን የሚያሳስበን ምክንያት ደግሞ በክርስቶስ ማን እንደሆንን፣ ቅዱስ የሆነውን ኑሮ እንኖር ዘንድ ኃይል የሆነልንና ወደፊት ዘላለምን ለመውረስ የምንችል ነን በማለት ነው፡፡

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ
6 ቀናት
ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡

መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
18 ቀናት
ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።