ኦሪት ዘፍጥረት 10

10
1የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኍላ ልጆች ተወለዱላቸው። 2የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። 3የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። 4የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው። 5ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። 6የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፋጥ፥ ከነዓን ናቸው። 7የኩሽም ልጆች ሳባ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። 8ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያክክ መሆንን ጀመረ። 9እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። 10የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን ኦሬክ አርካድ ካልኔ ናቸው። 11አሦርም ከዚያች አገር ወጣ ነነዌን የረሆቦትን ከተማ፥ 12ካለህን በነነዌና በካለህ መካከለም ሬሴንን ሠራ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት። 13ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥ 14ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ።
15ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ 16ኬጢያውያንንም፥ ኢያብጅሳውያንንም፥ አሞራውያንንም፥ 17ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም፥ 18ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኍላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። 19የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ስረስ ነው ወደ ሰዶምና ወድደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣድረስ ነው። 20የካም ልጆች በየነገድዳቸውና በየቋንቋቸው በየምድራችውን በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።
21ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዳለት እርሱም የያፌት ታላቅ ወምድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው። 22የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው። 23የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው። 24አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ። 25ለዔቦርን ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዩቅጣን ነው። 26ዩቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥ 27ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥ 28ደቅላንም ዖበልን፥ አቢማኤልንም፥ 29ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዩቅጣን ልጆች ናቸው። 30ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። 31የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባችው እነዚህ ናቸው።
32የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኍላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተክከፋፈሉ።

Kleurmerk

Deel

Kopieer

None

Wil jy jou kleurmerke oor al jou toestelle gestoor hê? Teken in of teken aan

Video vir ኦሪት ዘፍጥረት 10