የሉ​ቃስ ወን​ጌል 5

5
ስለ ስም​ዖ​ንና ስለ ዘብ​ዴ​ዎስ ልጆች መጠ​ራት
1ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር። 2በባ​ሕ​ሩም ዳር ሁለት ታን​ኳ​ዎች ቁመው አየ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዓሣ አጥ​ማ​ጆች መረ​ባ​ቸ​ውን ሊያ​ጥቡ ወረዱ። 3#ማቴ. 13፥1-2፤ ማር. 3፥9-10፤ 4፥1። ከሁ​ለቱ ታን​ኳ​ዎች ወደ አን​ዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺ​ውም ታንኳ የስ​ም​ዖን ነበ​ረች፤ “ከም​ድር ጥቂት እልፍ አድ​ር​ጋት” አለው፤ በታ​ን​ኳ​ዪ​ቱም ውስጥ ተቀ​ምጦ ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው። 4ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው። 5#ዮሐ. 21፥3። ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “መም​ህር፥ ሌሊ​ቱን ሁሉ ደክ​መ​ናል፤ የያ​ዝ​ነ​ውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘ​ዝ​ኸን መረ​ቦ​ቻ​ች​ንን እን​ጥ​ላ​ለን” አለው። 6#ዮሐ. 21፥6። እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸ​ውም ባደ​ረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስ​ኪ​ቀ​ደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ። 7መጥ​ተ​ውም ይረ​ዱ​አ​ቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነ​በ​ሩ​ትን ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም እስ​ኪ​ጠ​ልቁ ድረስ ሁለ​ቱን ታን​ኳ​ዎች ሞሉ። 8ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው። 9እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ስለ ተያ​ዘው ዓሣ ተደ​ን​ቀው ነበ​ርና። 10እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው። 11ታን​ኳ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አወ​ጡና ሁሉን ትተው ተከ​ተ​ሉት።
ለም​ጻ​ሙን ስለ ማዳኑ
12በአ​ን​ዲት ከተማ ሳለም ሁለ​መ​ናው ለም​ጻም የሆነ ሰው መጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ በፊቱ ወድቆ ሰገ​ደ​ለ​ትና፥ “አቤቱ ብት​ወ​ድስ ልታ​ነ​ጻኝ ትች​ላ​ለህ” እያለ ማለ​ደው። 13እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው። 14#ዘሌ. 14፥1-32። ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገር ከለ​ከ​ለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስ​ህን ለካ​ህን አስ​መ​ር​ምር፤ ምስ​ክ​ርም ይሆ​ን​ባ​ቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባ​ህን አቅ​ርብ” ብሎ አዘ​ዘው። 15ዜና​ውም በሁሉ ተሰማ፤ ብዙ ሰዎ​ችም ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ ይመጡ ነበር። 16እርሱ ግን ወደ ምድረ በዳ እየ​ወጣ ይጸ​ልይ ነበር።
ስለ መጻ​ጒዕ መፈ​ወስ
17ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ። 18እነሆ፥ ሰዎች በአ​ልጋ ተሸ​ክ​መው ሽባ የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰ​ውም ወደ እርሱ ሊያ​ስ​ገ​ቡት ወደዱ። 19ሰውም ተጨ​ና​ንቆ ነበ​ርና የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​በት አጡ፤ ወደ ሰገ​ነ​ትም ወጡ፤ ጣራ​ው​ንም አፍ​ር​ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ፊት ከነ​አ​ል​ጋው አወ​ረ​ዱት። 20እም​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም አይቶ ያን ሰው፥ “ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለው። 21ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር። 22ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ? 23ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ ከማ​ለ​ትና ተነ​ሥ​ተህ ሂድ ከማ​ለት ማና​ቸው ይቀ​ላል? 24ለሰው ልጅ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው እን​ድ​ታ​ውቁ፤ ያን ሽባ፦ ተነ​ሣና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ወደ ቤትህ ሂድ ብዬ​ሃ​ለሁ” አለው። 25ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥቶ ተኝ​ቶ​በት የነ​በ​ረ​ውን አልጋ በፊ​ታ​ቸው ተሸ​ክሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገነ ወደ ቤቱ ሄደ። 26ሁሉም ተደ​ነቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እጅ​ግም እየ​ፈሩ፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን” አሉ።
ስለ ቀራጩ ሌዊ መጠ​ራት
27ከዚ​ህም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ሌዊ የሚ​ባል ቀራጭ ሰው በቀ​ረጥ መቀ​በ​ያው ቦታ ተቀ​ምጦ አየና፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው። 28ሁሉ​ንም ተወና ተነ​ሥቶ ተከ​ተ​ለው። 29ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደ​ረ​ገ​ለት፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለምሳ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ሌሎ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ። 30#ሉቃ. 15፥1-2። ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ። 31ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትን በሽ​ተ​ኞች እንጂ ጤነ​ኞች አይ​ሹ​ትም። 32ኃጥ​ኣ​ንን ወደ ንስሓ እንጂ ጻድ​ቃ​ንን ልጠራ አል​መ​ጣ​ሁም።”
ስለ ጾም
33እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት። 34ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሙ​ሽ​ራው ሚዜ​ዎች ሙሽ​ራው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለ መጾም አይ​ች​ሉም። 35ነገር ግን ሙሽ​ራ​ውን ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊ​ዜም ይጾ​ማሉ።” 36በም​ሳ​ሌም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በአ​ሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአ​ዲስ ልብስ እራፊ የሚ​ጥፍ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን አዲሱ አሮ​ጌ​ውን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ አዲሱ እራ​ፊም ከአ​ሮ​ጌው ጋር አይ​ስ​ማ​ማም። 37አዲስ ጠጅ​ንም በአ​ሮጌ ረዋት የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ ወይ​ኑም ይፈ​ስ​ሳል፤ ረዋ​ቱም ይቀ​ደ​ዳል። 38ነገር ግን አዲ​ሱን ጠጅ በአ​ዲስ ረዋት ያደ​ር​ጉ​ታል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይጠ​ባ​በ​ቃሉ። 39የከ​ረ​መ​ውን የወ​ይን ጠጅ ሊጠጣ ወድዶ አዲ​ሱን የሚሻ የለም፤ የከ​ረ​መው ይሻ​ላል ይላ​ልና።”

Kleurmerk

Deel

Kopieer

None

Wil jy jou kleurmerke oor al jou toestelle gestoor hê? Teken in of teken aan