የሉቃስ ወንጌል 3:4-6
የሉቃስ ወንጌል 3:4-6 አማ2000
በምድረ በዳ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እንዲህ ሲል፥ “የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፤ ጥርጊያውንም አስተካክሉ። ጐድጓዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራራውም፥ ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰንከልካላውም የቀና ጥርጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መንገድም ይስተካከል። ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትድግና ይይ።”