1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰዉን በመልኩ ፈጠረ በእግአብሔር መልክ ፈጠራቸዉ።
Vergelyk
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ስማይንና ምድርን ፈጠረ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ስፍፎ ነበር።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገዉን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኚ ቀን።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለዉን ሐመለማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራዉንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራዉ። ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's