1
የዮሐንስ ወንጌል 8:12
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።
Qhathanisa
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:12
2
የዮሐንስ ወንጌል 8:32
እውነትንም ታውቋታላችሁ፤ እውነትም አርነት ታወጣችኋለች።”
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:32
3
የዮሐንስ ወንጌል 8:31
ጌታችን ኢየሱስም ያመኑበትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተም በቃሌ ጸንታችሁ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:31
4
የዮሐንስ ወንጌል 8:36
ወልድ አርነት ካወጣችሁ በእውነት አርነት የወጣችሁ ናችሁ።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:36
5
የዮሐንስ ወንጌል 8:7
ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:7
6
የዮሐንስ ወንጌል 8:34
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢኣትን የሚሠራ ሁሉ የኀጢኣት ባርያ ነው።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:34
7
የዮሐንስ ወንጌል 8:10-11
ጌታችን ኢየሱስም ቀና ብሎ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚከሱሽ ወዴት አሉ?” እርስዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማየው የለም” ብላ መለሰችለት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ ኀጢኣት አትሥሪ” አላት።
Hlola የዮሐንስ ወንጌል 8:10-11
Ikhaya
IBhayibheli
Amapulani
Amavidiyo