1
ሉቃስ 13:24
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
“በጠባቡ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ እላችኋለሁ፤ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም።
Qhathanisa
Hlola ሉቃስ 13:24
2
ሉቃስ 13:11-12
በዚያም የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጕበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ “አንቺ ሴት፤ ከሕመምሽ ነጻ ወጥተሻል” አላት፤
Hlola ሉቃስ 13:11-12
3
ሉቃስ 13:13
እጁንም በላይዋ ጫነ፤ እርሷም ወዲያው ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
Hlola ሉቃስ 13:13
4
ሉቃስ 13:30
እነሆ፤ ከኋለኞች መካከል ፊተኞች የሚሆኑ፣ ከፊተኞች መካከልም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።”
Hlola ሉቃስ 13:30
5
ሉቃስ 13:25
የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደ ሆናችሁና ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።
Hlola ሉቃስ 13:25
6
ሉቃስ 13:5
አይደለም፣ እላችኋለሁ፤ ንስሓ ካልገባችሁ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።”
Hlola ሉቃስ 13:5
7
ሉቃስ 13:27
“እርሱም፣ ‘እላችኋለሁ፤ አላውቃችሁም ከየት እንደ መጣችሁም አላውቅም፤ እናንተ ዐመፀኞች ሁሉ ከእኔ ራቁ’ ይላል።
Hlola ሉቃስ 13:27
8
ሉቃስ 13:18-19
ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች? ከምንስ ጋራ ላመሳስላት? አንድ ሰው ወስዶ በዕርሻው ውስጥ የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ አድጋ ዛፍ ሆነች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቿ ላይ ሰፈሩ።”
Hlola ሉቃስ 13:18-19
Ikhaya
IBhayibheli
Amapulani
Amavidiyo