1
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
对照
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
2
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
እንዲህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድዶአልና ልቀቀኝ።” እርሱም “ከአልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
3
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
4
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
5
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
6
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
እንዲህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እርሱም፥ “ያዕቆብ ነኝ” አለው።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
7
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
ያዕቆብም፥ “ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ድንቅ ነውና” አለው።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
8
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
9
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ አደንዝዞአልና።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
10
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
ያዕቆብም አለ፥ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፤ በጎነትንም አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፥
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
11
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
探索 ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
主页
圣经
计划
视频