1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።
موازنہ
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኳችሁንም ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
“እኔን የሚወደኝ ትእዛዜን የሚቀበልና በሥራ ላይ የሚያውለው ነው፤ እኔንም የሚወደኝን አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔ አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል። ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ ምክንያት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ፤
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:15
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ አለበለዚያ ግን ‘የምትኖሩበትን ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ’ ባልኳችሁ ነበር።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄ ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ እኔ ባለሁበት እንድትኖሩ እንደገና መጥቼ እወስዳችኋለሁ።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስ “ጌታ ሆይ! ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ ታዲያ፥ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው።
تلاش የዮሐንስ ወንጌል 14:5
صفحہ اول
بائبل
مطالعاتی منصوبہ
Videos