1
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ጋር ለምገባው ለዚህ ለዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ፥ ቀስቴን በደመናዎች ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም ቀስት ከምድር ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ይኖራል።
موازنہ
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
2
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
3
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
4
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ፥ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
5
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
ከዚህ በፊት የአትክልት ዐይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ።
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
7
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
“እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።”
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
صفحہ اول
بائبل
مطالعاتی منصوبہ
Videos