1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።
Karşılaştır
የዮሐንስ ወንጌል 15:5 keşfedin
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:4 keşfedin
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:7 keşfedin
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:16 keşfedin
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:13 keşfedin
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:2 keşfedin
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:12 keşfedin
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:8 keşfedin
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤
የዮሐንስ ወንጌል 15:1 keşfedin
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:6 keşfedin
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:11 keşfedin
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:10 keşfedin
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:17 keşfedin
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:19 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar