1
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በእርሳችሁ ከተዋደዳችሁ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰው ሁሉ ያውቃል።”
Karşılaştır
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35 keşfedin
2
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15
እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁት እናንተም እንድታደርጉ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15 keşfedin
3
የዮሐንስ ወንጌል 13:7
ኢየሱስም “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 13:7 keşfedin
4
የዮሐንስ ወንጌል 13:16
እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላኪው አይበልጥም።
የዮሐንስ ወንጌል 13:16 keşfedin
5
የዮሐንስ ወንጌል 13:17
ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:17 keşfedin
6
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5
ስለዚህ ከማእድ ተነሣና ልብሱን አስቀመጠ፤ ማበሻ ጨርቅም አንሥቶ በወገቡ ታጠቀ። ከዚህ በኋላ በመታጠቢያ ዕቃ ውሃ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብ ጀመረ፤ በታጠቀውም ማበሻ ጨርቅ እግራቸውን አበሰ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar