የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 7

7
ወደ ገሊላ ስለ መሄዱ
1ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና። 2#ዘሌ. 23፥34፤ ዘዳ. 16፥13። የአ​ይ​ሁ​ድም የዳስ በዓ​ላ​ቸው ደርሶ ነበር። 3ወን​ድ​ሞ​ቹም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አሉት- “ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትህ የም​ት​ሠ​ራ​ውን ሥራ​ህን እን​ዲ​ያዩ ከዚህ ወጥ​ተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ። 4ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ። 5ወን​ድ​ሞቹ ገና አላ​መ​ኑ​በ​ትም ነበ​ርና። 6ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ የእ​ና​ንተ ጊዜ ግን ዘወ​ትር የተ​ዘ​ጋጀ ነው። 7ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና። 8እና​ን​ተም ወደ​ዚህ በዓል ውጡ፤ እኔ አሁን ወደ​ዚህ በዓል አል​ወ​ጣም፤ ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰ​ምና።” 9እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ​አ​ቸው በገ​ሊላ ቀረ።
ወደ በዓል ስለ መው​ጣቱ
10ወን​ድ​ሞቹ ለበ​ዓል ከወጡ በኋላ፥ እር​ሱም ያን​ጊዜ በግ​ልጥ ሳይ​ሆን ተሰ​ውሮ ወጣ። 11አይ​ሁ​ድም፥ “ያ ወዴት ነው?” እያሉ በበ​ዓሉ ይፈ​ል​ጉት ጀመር። 12ሕዝ​ቡም ስለ እርሱ ብዙ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፥ “ደግ ሰው ነው” ያሉ ነበሩ፤ ሌሎች ግን፥ “አይ​ደ​ለም፤ ሕዝ​ቡን ያስ​ታል እንጂ” አሉ። 13ነገር ግን፥ አይ​ሁ​ድን በመ​ፍ​ራት የእ​ር​ሱን ነገር ገልጦ የተ​ና​ገረ አል​ነ​በ​ረም።
በበ​ዓሉ ላይ ስለ ማስ​ተ​ማሩ
14በበ​ዓሉ ቀኖች እኩ​ሌ​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ መቅ​ደስ ወጥቶ ያስ​ተ​ምር ጀመረ። 15አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ሳይ​ማር መጽ​ሐ​ፍን እን​ዴት ያው​ቃል?” እያሉ ትም​ህ​ር​ቱን#“ትም​ህ​ር​ቱን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አደ​ነቁ። 16ስለ​ዚ​ህም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትም​ህ​ርቴ የላ​ከኝ ናት እንጂ የእኔ አይ​ደ​ለ​ችም። 17ፈቃ​ዱን ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ወ​ድድ ግን ትም​ህ​ርቴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የም​ና​ገ​ረ​ውም ከራሴ እን​ዳ​ይ​ደለ እርሱ ያው​ቃል። 18ከራሱ የሚ​ና​ገር የራ​ሱን ክብር ይሻል፤ የላ​ከ​ውን ያከ​ብር ዘንድ የሚ​ፈ​ልግ ግን እው​ነ​ተኛ ነው፤ ሐሰ​ትም የለ​በ​ትም። 19ሙሴ ኦሪ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ የለ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንዱ ስንኳ ኦሪ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ እን​ግ​ዲህ ልት​ገ​ድ​ሉኝ ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?” 20ሕዝ​ቡም፥ “ጋኔን አለ​ብ​ህን? ማን ሊገ​ድ​ልህ ይሻል?” ብለው መለ​ሱ​ለት። 21ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “አንድ ሥራ ሠራሁ፤ ሁላ​ች​ሁም አደ​ነ​ቃ​ችሁ። 22#ዘፍ. 17፥10፤ ዘሌ. 12፥3። ስለ​ዚህ ሙሴ ግዝ​ረ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ቶች ናት እንጂ ከሙሴ አይ​ደ​ለ​ችም፤ በሰ​ን​በ​ትም ሰውን ትገ​ዝ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ። 23#ዮሐ. 5፥9። የሙሴ ሕግ እን​ዳ​ይ​ሻር ሰው በሰ​ን​በት የሚ​ገ​ዘር ከሆነ እን​ግ​ዲያ ሰውን ሁለ​ን​ተ​ና​ውን በሰ​ን​በት ባድ​ነው ለምን ትነ​ቅ​ፉ​ኛ​ላ​ችሁ? 24የእ​ው​ነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማ​ድ​ላት አት​ፍ​ረዱ።”
ስለ ሕዝቡ ዋይታ
25ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎ​ችም እን​ዲህ የሚሉ ነበሩ፥ “ይህ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት የሚ​ሹት አይ​ደ​ለ​ምን? 26እነሆ፥ እርሱ በገ​ሀድ ይና​ገ​ራል፤ እነ​ርሱ ግን ምንም የሚ​ሉት የለም፤ ይህ በእ​ው​ነት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ምና​ል​ባት አለ​ቆች ዐው​ቀው ይሆን? 27ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜስ ከወ​ዴት እንደ ሆነ ማንም አያ​ው​ቅም”። 28ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ። 29እኔ ግን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እኔ ከእ​ርሱ ነኝና፥ እር​ሱም ልኮ​ኛ​ልና። 30ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና። 31ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በ​ትና፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይህ ሰው ካደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የሚ​በ​ልጥ ያደ​ር​ጋ​ልን?” አሉ።
ፈሪ​ሳ​ው​ያን ሊይ​ዙት ሎሌ​ዎ​ችን እንደ ላኩ
32ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ። 33ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ቀን አብ​ሬ​አ​ችሁ እኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ላከኝ እሄ​ዳ​ለሁ። 34ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም።” 35አይ​ሁ​ድም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ አሉ፥ “እኛ ልና​ገ​ኘው የማ​ን​ችል ይህ ወዴት ይሄ​ዳል? ወይስ የግ​ሪ​ክን ሰዎች ለማ​ስ​ተ​ማር በግ​ሪክ ሀገር ወደ ተበ​ተ​ኑት ይሄ​ዳ​ልን? 36‘ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም’ የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድን ነው?”
ስለ መን​ፈስ ቅዱስ
37 # ዘሌ. 23፥36። በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ በታ​ላ​ቅዋ የበ​ዓል ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ቆመና ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “የተ​ጠማ ወደ እኔ ይም​ጣና ይጠጣ። 38#ሕዝ. 47፥1፤ ዘካ. 14፥8። በእ​ኔም የሚ​ያ​ምን መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የሕ​ይ​ወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈ​ስ​ሳል።” 39ይህ​ንም የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሰዎች ይቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ተና​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገና ስላ​ል​ከ​በረ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና።
በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ስለ ሆነው መለ​ያ​የት
40ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ሰም​ተው “በእ​ው​ነት ይህ ነቢይ ነው” አሉ። 41“ክር​ስ​ቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አሉ፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ ከገ​ሊላ ይወ​ጣ​ልን? 42#2ሳሙ. 7፥12፤ ሚክ. 5፥2። መጽ​ሐፍ ‘ክር​ስ​ቶስ ከዳ​ዊት ዘርና ከዳ​ዊት ከተማ ከቤተ ልሔም ይመ​ጣል’ ይል የለ​ምን?” 43ስለ እር​ሱም ሕዝቡ እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ። 44ከእ​ነ​ር​ሱም ሊይ​ዙት የወ​ደዱ ነበሩ፤ ነገር ግን በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነሣ የለም።
45ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው። 46ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም መል​ሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተና​ገ​ረው ያለ ከቶ ሰው አል​ተ​ና​ገ​ረም” አሉ​አ​ቸው። 47ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ን​ተም ደግሞ ተሳ​ሳ​ታ​ች​ሁን? 48ከአ​ለ​ቆች ወይም ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ያመ​ነ​በት አለን? 49ኦሪ​ትን ከማ​ያ​ውቁ ከእ​ነ​ዚህ ስሑ​ታን ሕዝብ በቀር፤ እነ​ር​ሱም የተ​ረ​ገሙ ናቸው።” 50#ዮሐ. 3፥1-2። ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሄ​ደው ኒቆ​ዲ​ሞስ እን​ዲህ አላ​ቸው። 51“ሕጋ​ችን አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ሰማ፤ የሠ​ራ​ው​ንም ሳያ​ውቅ በሰው ይፈ​ር​ዳ​ልን?” 52እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት። 53ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ቤታ​ቸው ሄዱ።

ที่ได้เลือกล่าสุด:

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 7: አማ2000

เน้นข้อความ

แบ่งปัน

คัดลอก

None

ต้องการเน้นข้อความที่บันทึกไว้ตลอดทั้งอุปกรณ์ของคุณหรือไม่? ลงทะเบียน หรือลงชื่อเข้าใช้