1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም።
เปรียบเทียบ
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይደንግጥ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለ የሚጠብቀውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ ይልክላችኋል። እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ይኖራልና፤ ያድርባችሁማልና።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ ይከብር ዘንድ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ያን አደርግላችኋለሁ።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:15
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያና ማረፊያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ቦታ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበር።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የምትሄድበትን የማናውቅ እንግዲህ መንገዱን እንዴት እናውቃለን?” አለው።
สำรวจ የዮሐንስ ወንጌል 14:5
หน้าหลัก
พระคัมภีร์
แผนการอ่านต่างๆ
วิดีโอ