የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 3

3
ፈሪ​ሳ​ዊው ናቆ​ዲ​ሞስ ወደ ኢየ​ሱስ ስለ መም​ጣቱ
1ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን የአ​ይ​ሁድ አለቃ የሆነ ኒቆ​ዲ​ሞስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ። 2እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።” 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው። 4ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም፥ “ሰው ከሸ​መ​ገለ በኋላ ዳግ​መኛ መወ​ለድ እን​ደ​ምን ይች​ላል? ዳግ​መኛ ይወ​ለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ልሶ መግ​ባት ይች​ላ​ልን?” አለው። 5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም። 6ከሥጋ የተ​ወ​ለደ ሥጋ ነውና፤ ከመ​ን​ፈ​ስም የተ​ወ​ለደ መን​ፈስ ነውና። 7ስለ​ዚ​ህም ዳግ​መኛ ልት​ወ​ለዱ ይገ​ባ​ች​ኋል ስለ አል​ሁህ አታ​ድ​ንቅ። 8ነፋስ ወደ ወደ​ደው ይነ​ፍ​ሳ​ልና፤ ድም​ፁ​ንም ትሰ​ማ​ለህ፤ ነገር ግን ከየት እን​ደ​ሚ​መጣ ወዴ​ትም እን​ደ​ሚ​ሄድ አታ​ው​ቅም፤ ከመ​ን​ፈስ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ እን​ዲሁ ነው።” 9ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መልሶ፥ “ይህ ሊሆን እን​ዴት ይቻ​ላል?” አለው። 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መም​ህ​ራ​ቸው ነህ፤ ነገር ግን እን​ዴት ይህን አታ​ው​ቅም?” አለው። 11እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ የም​ና​ው​ቀ​ውን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ያየ​ነ​ው​ንም እን​መ​ሰ​ክ​ራ​ለን፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን አት​ቀ​በ​ሉ​ንም። 12በም​ድር ያለ​ውን ስነ​ግ​ራ​ችሁ ካላ​መ​ና​ች​ሁኝ#በግ​ሪኩ “... ካላ​መ​ና​ችሁ ... እን​ዴት ታም​ና​ላ​ችሁ” ይላል። በሰ​ማይ ያለ​ውን ብነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ዴት ታም​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? 13ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው። 14#ዘኍ​. 21፥9። ሙሴ በም​ድረ በዳ እባ​ቡን እንደ ሰቀ​ለው የሰው ልጅ እን​ዲሁ ይሰ​ቀል ዘንድ አለው። 15ያመ​ነ​በት ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ እን​ዲ​ኖር እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ። 16በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና። 17ዓለም በእ​ርሱ ይድን ዘንድ ነው እንጂ በዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ወደ​ዚህ ዓለም አል​ላ​ከ​ው​ምና። 18በእ​ርሱ ያመነ አይ​ፈ​ረ​ድ​በ​ትም፤ በእ​ርሱ ያላ​መነ ግን ፈጽሞ ተፈ​ር​ዶ​በ​ታል፤ በአ​ንዱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ስም አላ​መ​ነ​ምና። 19ፍር​ዱም ይህ ነው፤ ብር​ሃን ወደ ዓለም መጥ​ቶ​አ​ልና፤ ሰውም ሥራው ክፉ ስለ​ሆነ ከብ​ር​ሃን ይልቅ ጨለ​ማን መር​ጦ​አ​ልና። 20ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ#በግ​ሪኩ “ክፉም ስለ​ሆነ ...” አይ​ልም። ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም። 21እው​ነ​ትን የሚ​ሠራ ግን ሥራው ይገ​ለጥ ዘንድ ወደ ብር​ሃን ይመ​ጣል፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ይሠ​ራ​ልና።
ጌታ​ችን ወደ ይሁዳ ምድር ስለ መሄዱ
22ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም እያ​ጠ​መቀ አብ​ሮ​አ​ቸው ተቀ​መጠ። 23ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ#“በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር። 24#ማቴ. 14፥3፤ ማር. 6፥17፤ ሉቃ. 3፥19-20። ዮሐ​ንስ ገና ወደ ወኅኒ ቤት አል​ገ​ባም ነበ​ርና።
ስለ ማን​ጻት የተ​ደ​ረገ ክር​ክር
25ከዚ​ህም በኋላ በዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ስለ ማን​ጻት ክር​ክር ሆነ፤ 26ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት። 27ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ሰው ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠው በስ​ተ​ቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገን​ዘብ ሊያ​ደ​ርግ ምንም አይ​ች​ልም። 28#ዮሐ. 1፥20። እኔ ክር​ስ​ቶስ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እን​ድ​ሰ​ብ​ክ​ለት#“እን​ድ​ሰ​ብ​ክ​ለት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ከእ​ርሱ በፊት ተል​ኬ​አ​ለሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ። 29ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች። 30የእ​ርሱ ትበ​ዛ​ለች፤ የእኔ ግን ታንስ ዘንድ ይገ​ባል።”
31ከላይ የመ​ጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከም​ድር የተ​ገ​ኘ​ውም ምድ​ራዊ ነው፤ የም​ድ​ሩ​ንም ይና​ገ​ራል፤ ከሰ​ማይ የመ​ጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው። 32ባየ​ውና በሰ​ማው ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የሚ​ቀ​በ​ለው የለም። 33ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን የተ​ቀ​በለ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ አተመ። 34እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይና​ገ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን ሰፍሮ አይ​ሰ​ጥ​ምና። 35#ማቴ. 11፥27፤ ሉቃ. 10፥22። አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው። 36በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።

Märk

Dela

Kopiera

None

Vill du ha dina höjdpunkter sparade på alla dina enheter? Registrera dig eller logga in