የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 15

15
ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ ስለ መሆኑ
1“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው። 2በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል። 3እና​ንተ ግን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ቃል ፈጽ​ማ​ችሁ ንጹ​ሓን ናችሁ። 4በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም። 5እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና። 6በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል። 7በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል። 8ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል። 9አብ እንደ ወደ​ደኝ እን​ዲሁ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ፤ በፍ​ቅ​ሬም ኑሩ። 10የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። 11ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስ​ታ​ች​ሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።
12 # ዮሐ. 13፥34፤ 15፥17፤ 1ዮሐ. 3፥23፤ 2ዮሐ. 5። “እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ድ​ቷ​ደዱ የእኔ ትእ​ዛዝ ይህች ናት። 13ስለ ወዳ​ጆቹ ሕይ​ወ​ቱን አሳ​ልፎ የሚ​ሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ፍቅር የለም። 14እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ። 15እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና። 16እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ። 17እርስ በር​ሳ​ች​ሁም እን​ድ​ቷ​ደዱ ይህን አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።
ዓለም የጌ​ታን ተከ​ታ​ዮች እን​ደ​ሚ​ጠላ
18“ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ። 19እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል። 20#ማቴ. 10፥24፤ ሉቃ. 6፥40፤ ዮሐ. 13፥16። እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር። 21ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና። 22ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም። 23እኔን የሚ​ጠላ አባ​ቴን ይጠ​ላል። 24ሌላ ያል​ሠ​ራ​ውን ሥራ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ባል​ሠራ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን እኔ​ንም አባ​ቴ​ንም አይ​ተ​ዋል፤ ጠል​ተ​ው​ማል። 25ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።
መን​ፈስ ቅዱስ ከአብ ስለ​መ​ሥ​ረፁ
26“እኔ ከአብ ዘንድ የም​ል​ክ​ላ​ችሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እር​ሱም ከአብ የሚ​ወጣ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመ​ሰ​ክ​ራል። 27እና​ን​ተም ትመ​ሰ​ክ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራ​ች​ኋ​ልና።

Märk

Dela

Kopiera

None

Vill du ha dina höjdpunkter sparade på alla dina enheter? Registrera dig eller logga in