Mufananidzo weYouVersion
Mucherechedzo Wekutsvaka

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 14

14
አብ​ራም ሎጥን ከም​ርኮ እንደ መለ​ሰው
1በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤ 2ከሰ​ዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገ​ሞራ ንጉሥ ከበ​ርሳ፥ ከአ​ዳማ ንጉሥ ከሰ​ና​አር፥ ከሲ​ባዮ ንጉሥ ከሲ​ም​ቦር፤ ሴጎር ከተ​ባ​ለች ከባላ ንጉ​ሥም ጋር ጦር​ነት አደ​ረጉ። 3እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው። 4ዐሥራ ሁለት ዓመት ለኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር ተገዙ፤ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዐመፁ። 5በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ 6በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው። 7ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው። 8የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤ 9ከኤ​ላም ንጉሥ ከኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ ከአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ከቴ​ሮ​ጋል፥ ከሰ​ና​ዖር ንጉሥ ከአ​ሜ​ሮ​ፌል፥ ከእ​ላ​ሳር ንጉሥ ከአ​ር​ዮክ ጋር ተጋ​ጠሙ። እነ​ዚህ አራቱ ነገ​ሥ​ታት ከአ​ም​ስቱ ነገ​ሥ​ታት ጋር ተዋጉ። 10ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤#ግእዙ “በዚ​ያም ገደ​ሉ​አ​ቸው” የሚል አለው። የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ። 11የሰ​ዶ​ም​ንና የገ​ሞ​ራን ፈረ​ሶች ሁሉ፥ ስን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይዘው ሄዱ። 12እነ​ር​ሱም የአ​ብ​ራ​ምን የወ​ን​ድም ልጅ ሎጥ​ንና ገን​ዘ​ቡን ይዘው ሄዱ። እርሱ በሰ​ዶም ይኖር ነበ​ርና።
13ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤#ግእዙ በብዙ ቍጥር ይጽ​ፋል። ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር። 14አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው። 15እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው። 16የሰ​ዶ​ምን ፈረ​ሶች ሁሉ አስ​መ​ለሰ፤ ደግ​ሞም የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥ​ንና ንብ​ረ​ቱን፥ ሴቶ​ች​ንና ሕዝ​ቡ​ንም አስ​መ​ለሰ።
መል​ከ​ጼ​ዴቅ አብ​ራ​ምን እንደ ባረ​ከው
17ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ር​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሥ​ታት ወግቶ ከተ​መ​ለ​ሰም በኋላ የሰ​ዶም ንጉሥ የን​ጉሥ ሜዳ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀ​በ​ለው ወጣ። 18የሳ​ሌም ንጉሥ መልከ ጼዴ​ቅም እን​ጀ​ራ​ንና የወ​ይን ጠጅን አወጣ፤ እር​ሱም የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን ነበረ። 19አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤ 20ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ የጣ​ለ​ልህ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቡሩክ ነው” አለው። አብ​ራ​ምም ከሁሉ ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው። 21የሰ​ዶም ንጉ​ሥም አብ​ራ​ምን፥ “ሰዎ​ቹን ስጠኝ፤ ፈረ​ሶ​ቹን#ግእዙ “ጥሪ​ትን” ይላል። ግን ለአ​ንተ ውሰድ” አለው። 22አብ​ራ​ምም የሰ​ዶ​ምን ንጉሥ አለው፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ወደ ፈጠረ ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ 23አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥ 24ብላ​ቴ​ኖች ከበ​ሉት እህ​ልና ከእኔ ጋር ከመ​ጡት ድርሻ በቀር፥ አው​ናን፥ ኤስ​ኮ​ልም፥ መም​ሬም እነ​ርሱ ድር​ሻ​ቸ​ውን ይው​ሰዱ።”

Sarudza vhesi

Pakurirana nevamwe

Sarudza zvinyorwa izvi

None

Unoda kuti zviratidziro zvako zvichengetedzwe pamidziyo yako yose? Nyoresa kana kuti pinda