Logotip YouVersion
Search Icon

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 6

6
የሰ​ዎች ክፋት
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰዎች በም​ድር ላይ መብ​ዛት በጀ​መሩ ጊዜ መልከ መል​ካ​ሞች ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው፤ 2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መን​ፈሴ በሰው ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸ​ውና፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆ​ናል” አለ። 4በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በም​ድር ላይ በመ​ፍ​ጠሩ ተጸ​ጸተ፤ በል​ቡም አዘነ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ። 8ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።
ኖኅ
9የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።#ዕብ. “ኖኅም አካ​ሄ​ዱን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አደ​ረገ” ይላል። 10ኖኅም ሦስት ልጆ​ችን ሴምን፥ ካምን ያፌ​ት​ንም ወለደ። 11ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተበ​ላ​ሸች፤ ምድ​ርም ግፍን ተመ​ላች። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደር​ሶ​አል፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ምድር በግፍ ተመ​ል​ታ​ለ​ችና፤ እኔም እነሆ፥ ከም​ድር ጋር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። 14ባለ አራት መዓ​ዝን የዕ​ን​ጨት መር​ከ​ብን ለአ​ንተ ሥራ፤ በመ​ር​ከ​ቢ​ቱም ክፍ​ሎ​ችን አድ​ርግ፤ በው​ስ​ጥም፥ በው​ጭም በቅ​ጥ​ራን ለቅ​ል​ቃት። 15መር​ከ​ብ​ዋ​ንም እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ታ​ለህ፤ የመ​ር​ከ​ቢቱ ርዝ​መት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወር​ድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍ​ታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። 16ለመ​ር​ከ​ቢ​ቱም መስ​ኮ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ከቁ​መ​ቷም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨር​ሳት፤ የመ​ር​ከ​ቢ​ቱ​ንም በር በጎ​ንዋ አድ​ርግ፤ ታች​ኛ​ው​ንም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ደርብ ታደ​ር​ግ​ላ​ታ​ለህ። 17እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል። 18ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ። 19ከእ​ን​ስሳ ሁሉ፥ ከተ​ን​ቀ​ሳ​ቃሽ አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ትመ​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወደ መር​ከብ ታገ​ባ​ለህ፤ ተባ​ትና እን​ስት ይሁን። 20ከወ​ፎች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከእ​ን​ስ​ሳም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ሳቡ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከአ​ንተ ጋር ይመ​ገቡ ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወን​ድና ሴት እየ​ሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። 21ከሚ​በ​ላ​ውም የመ​ብል ዓይ​ነት ሁሉ ለአ​ንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ እር​ሱም ለአ​ንተ፥ ለእ​ነ​ር​ሱም መብል ይሆ​ናል።” 22ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲሁ አደ​ረገ።

Označeno

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in