1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ጌታ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፥ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፥
Primerjaj
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፥ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፦ “የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “የሚስትህን የሦራን ስም ‘ሦራ’ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
Explore ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
Domov
Sveto pismo
Bralni načrti
Videoposnetki