1
የሉቃስ ወንጌል 21:36
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።”
Compară
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:36
2
የሉቃስ ወንጌል 21:34
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:34
3
የሉቃስ ወንጌል 21:19
በትዕግሥታችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ” አለ።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:19
4
የሉቃስ ወንጌል 21:15
ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:15
5
የሉቃስ ወንጌል 21:33
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:33
6
የሉቃስ ወንጌል 21:25-27
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ ከዚህም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ላይ ሆኖ ሲመጣ ሰዎች ያዩታል።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:25-27
7
የሉቃስ ወንጌል 21:17
ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:17
8
የሉቃስ ወንጌል 21:11
በየቦታውም ብርቱ የምድር መናወጥ፥ ራብና ወረርሽኝ ይሆናል። የሚያስፈሩ ነገሮችና ታላላቅ ምልክቶች በሰማይ ላይ ይታያሉ።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:11
9
የሉቃስ ወንጌል 21:9-10
ስለ ጦርነትና ስለ ሁከት በምትሰሙበት ጊዜም አትደንግጡ፤ አስቀድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ይሁን እንጂ ፍጻሜው ወዲያውኑ አይሆንም።” ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:9-10
10
የሉቃስ ወንጌል 21:25-26
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:25-26
11
የሉቃስ ወንጌል 21:10
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:10
12
የሉቃስ ወንጌል 21:8
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
Explorează የሉቃስ ወንጌል 21:8
Acasă
Biblia
Planuri
Videoclipuri