1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።” እግዚአብሔርም ሰውን በእግዚአብሔር አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
Compare
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፥ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚአብሔርም የፈጠረውን ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኛም ቀን ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚአብሔርም በብርሃኑና በጨለማው መካከል ለየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን፥” ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አንደኛ ቀንም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድር አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ ሐመልማሉ ሁሉ መብል ይሁንላችሁ።” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም “ምድር በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ ዘር የሚሰጥ ቡቃያን፥ በምድርም ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትንም ውኆች ለየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃም በመጠራቀሚያው ተሰበሰበ፤ የብሱም ተገለጠ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠራቀሚያውንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙም፤ የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ፥ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን፥ የምድር አራዊትንም እንደየወገኑ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፥ “ውኃ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችና በምድር ላይ ከሰማይ በታች የሚበርሩ አዕዋፍን ታስገኝ፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ