1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፥ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፥ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
Compare
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ