1
የሉቃስ ወንጌል 19:10
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው።”
Compare
የሉቃስ ወንጌል 19:10ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
2
የሉቃስ ወንጌል 19:38
እንዲህ ይሉም ነበር፤ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! ሰላም በሰማይ፥ ክብርም ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን!”
የሉቃስ ወንጌል 19:38ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
3
የሉቃስ ወንጌል 19:9
ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሰው ደግሞ የአብርሃም ዘር ነውና ዛሬ መዳን ለዚህ ቤት ሆኖአል፤
የሉቃስ ወንጌል 19:9ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
4
የሉቃስ ወንጌል 19:5-6
ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተና ዘኬዎስን፥ “ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በአንተ ቤት መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ከዛፉ ውረድ” አለው። ዘኬዎስም ቶሎ ብሎ ወረደና፥ በደስታ ኢየሱስን በቤቱ ተቀበለው።
የሉቃስ ወንጌል 19:5-6ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
5
የሉቃስ ወንጌል 19:8
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”
የሉቃስ ወንጌል 19:8ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
6
የሉቃስ ወንጌል 19:39-40
በሕዝቡ መካከል የነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ዝም አሰኛቸው!” አሉት። ኢየሱስም “እነርሱ እንኳ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ እላችኋለሁ” ሲል መለሰላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 19:39-40ਪੜਚੋਲ ਕਰੋ
Home
ਬਾਈਬਲ
Plans
ਵੀਡੀਓ