የሉ​ቃስ ወን​ጌል 20

20
ከሊ​ቃነ ካህ​ናት የቀ​ረበ ጥያቄ
1ከዚ​ህም በኋላ በአ​ንድ ቀን ሕዝ​ቡን በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው፥ ወን​ጌ​ል​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሡ​በት። 2“ይህን በማን ሥል​ጣን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ይህ​ንስ እን​ድ​ታ​ደ​ርግ ማን ፈቀ​ደ​ልህ? እስኪ ንገ​ረን” አሉት። 3እር​ሱም መልሶ፥ “እኔም አን​ዲት ነገ​ርን እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ንገ​ሩኝ፤ 4የዮ​ሐ​ንስ ጥም​ቀት ከወ​ዴት ናት? ከሰ​ማይ ናትን? ወይስ ከሰው?” አላ​ቸው። 5እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ ተባ​ባሉ፤ “ከሰ​ማይ ነው ብን​ለው ለምን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም? ይለ​ናል። 6ከሰው ነው ብን​ለ​ውም ሕዝቡ ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል፤ ሁሉም ዮሐ​ንስ ነቢይ እንደ ሆነ አም​ነ​ው​በ​ታ​ልና። 7ከወ​ዴት እንደ ሆነች አና​ው​ቅም” ብለው መለ​ሱ​ለት። 8ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም ይህን በማን ሥል​ጣን እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አል​ነ​ግ​ራ​ች​ሁም” አላ​ቸው።
ስለ ወይን ጠባ​ቂ​ዎች
9 # ኢሳ. 5፥1። ለሕ​ዝ​ቡም ይህን ምሳሌ ይመ​ስ​ል​ላ​ቸው ጀመረ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭ​መ​ቂ​ያም አስ​ቈ​ፈረ፤ ግን​ብም ሠራ​ለት፤#“መጭ​መ​ቂ​ያም አስ​ቈ​ፈረ ግን​ብም ሠ ራለት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ለገ​ባ​ሮ​ችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይ​መ​ለ​ስም ዘገየ። 10የመ​ከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባ​ሮቹ፥ ከወ​ይኑ ፍሬ ይል​ኩ​ለት ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ ገባ​ሮቹ ግን አገ​ል​ጋ​ዩን ደብ​ድ​በው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት። 11ዳግ​መ​ኛም ሌላ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም ደብ​ድ​በ​ውና አዋ​ር​ደው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት። 12ደግሞ ሦስ​ተ​ኛ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም አቍ​ስ​ለው ሰደ​ዱት። 13የወ​ይኑ ባለ​ቤ​ትም፦ እን​ግ​ዲህ ምን ላድ​ርግ? ምና​ል​ባት እር​ሱን እንኳ አይ​ተው ያፍሩ እንደ ሆነ የም​ወ​ደ​ውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው። 14ገባ​ሮ​ቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና ርስ​ቱን እን​ው​ሰድ ብለው ተማ​ከሩ። 15ከወ​ይኑ ቦታም ወደ ውጭ አው​ጥ​ተው ገደ​ሉት። 16የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ። 17#መዝ. 117፥22። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “ግን​በ​ኞች የና​ቁ​አት ድን​ጋይ እር​ስዋ የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነች፥ የሚ​ለው ጽሑፍ ምን​ድ​ነው? 18በዚ​ያች ድን​ጋይ ላይ የወ​ደቀ ሁሉ ይቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ እር​ስ​ዋም የወ​ደ​ቀ​ች​በ​ትን ታደ​ቅ​ቀ​ዋ​ለች።” 19ያን ጊዜም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎች ሊይ​ዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነ​ርሱ እንደ መሰለ ዐው​ቀ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ፈሩ​አ​ቸው።
ለቄ​ሣር ግብር ስለ መስ​ጠት
20ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ። 21እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ አንተ እው​ነት እን​ደ​ም​ት​ና​ገ​ርና እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ፊት አይ​ተ​ህም እን​ደ​ማ​ታ​ዳላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ በቀ​ጥታ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር እና​ው​ቃ​ለን። 22ለቄ​ሣር ግብር መስ​ጠት ይገ​ባል? ወይስ አይ​ገ​ባም?” 23ተን​ኰ​ላ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈ​ት​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ገን​ዘ​ቡን አሳ​ዩኝ” አላ​ቸው። 24አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት። 25እር​ሱም፥ “እን​ኪ​ያስ የቄ​ሣ​ርን ለቄ​ሣር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጡ” አላ​ቸው። 26በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በአ​ነ​ጋ​ገሩ ማሳ​ሳት ተሳ​ና​ቸው፤ መል​ሱ​ንም አድ​ን​ቀው ዝም አሉ።
ስለ ትን​ሣኤ ሙታን
27“ሙታን አይ​ነ​ሡም” ከሚሉ ከሰ​ዱ​ቃ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ። 28#ዘዳ. 25፥5። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል። 29እን​ግ​ዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግ​ብቶ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ። 30እን​ደ​ዚ​ሁም ሁለ​ተ​ኛው አገ​ባት፤ እር​ሱም ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ፤ 31ሦስ​ተ​ኛ​ውም አገ​ባት፤ እን​ዲ​ሁም ሰባቱ ሁሉ አገ​ቡ​አት፤ ልጅ ሳይ​ወ​ል​ዱም ሞቱ። 32ከሁ​ሉም በኋላ ያቺ ሴት ሞተች። 33እን​ግ​ዲህ ሙታን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ለማ​ን​ኛው ሚስት ትሆ​ና​ለች? ሰባ​ቱም ሁሉ አግ​ብ​ተ​ዋት ነበ​ርና።” 34ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገ​ባሉ፥ ይጋ​ባ​ሉም፤ ይወ​ል​ዳሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም።#“... ይወ​ል​ዳሉ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም ...” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 35ያን ዓለ​ምና የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ሊወ​ርሱ የሚ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚያ ግን አያ​ገ​ቡም፤ አይ​ጋ​ቡም። 36እን​ግ​ዲህ ወዲህ ሞት የለ​ባ​ቸ​ውም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ናቸው እንጂ፤ የት​ን​ሣኤ ልጆ​ችም ስለ​ሆኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ። 37#ዘፀ. 3፥6። ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል። 38እን​ኪ​ያስ የሕ​ያ​ዋን አም​ላክ እንጂ የሙ​ታን አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም በእ​ርሱ ዘንድ ሕያ​ዋን ናቸ​ውና።” 39ከጻ​ፎ​ችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መም​ህር ሆይ፥ መል​ካም ብለ​ሃል” ብለው መለሱ። 40ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ ማንም የለም።
ስለ መሲሕ የቀ​ረበ ጥያቄ
41እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ዴት የዳ​ዊት ልጅ ይሉ​ታል? 42እርሱ ራሱ ዳዊት በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘ጌታ ጌታ​ዬን በቀኜ ተቀ​መጥ፥ 43#መዝ. 109፥1። ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ጋ​ቸው ድረስ’ ብሏል። 44እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ዳዊት ‘ጌታዬ’ ያለው እን​ዴት ልጁ ይሆ​ናል?”
ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ስለ ማስ​ጠ​ን​ቀቁ
45ሕዝ​ቡም ሲሰሙ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው። 46“ልብ​ሳ​ቸ​ውን አን​ዘ​ር​ፍ​ፈው ወዲያ ወዲህ ማለ​ትን ከሚሹ፥ በገ​በያ እጅ መነ​ሣ​ት​ንና በአ​ደ​ባ​ባይ ፊት ለፊት፥ በማ​ዕ​ድም ጊዜ በከ​በ​ሬታ መቀ​መጫ መቀ​መ​ጥን ከሚ​ወዱ ጻፎች ተጠ​በቁ። 47የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”

Markering

Deel

Kopiëren

None

Wil je jouw markerkingen op al je apparaten opslaan? Meld je aan of log in