1
ዘፍጥረት 9:12-13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋራ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋራ፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Vergelijk
Ontdek ዘፍጥረት 9:12-13
2
ዘፍጥረት 9:16
ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔርና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”
Ontdek ዘፍጥረት 9:16
3
ዘፍጥረት 9:6
“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል፣ እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።
Ontdek ዘፍጥረት 9:6
4
ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤
Ontdek ዘፍጥረት 9:1
5
ዘፍጥረት 9:3
ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
Ontdek ዘፍጥረት 9:3
6
ዘፍጥረት 9:2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታትና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
Ontdek ዘፍጥረት 9:2
7
ዘፍጥረት 9:7
እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”
Ontdek ዘፍጥረት 9:7
Thuisscherm
Bijbel
Leesplannen
Video's