1
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ጋር ለምገባው ለዚህ ለዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ፥ ቀስቴን በደመናዎች ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም ቀስት ከምድር ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ይኖራል።
Bandingkan
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
2
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
3
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
4
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ፥ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
5
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
ከዚህ በፊት የአትክልት ዐይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ።
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
7
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
“እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።”
Selidiki ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
Halaman Utama
Alkitab
Pelan
Video