ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 6:1-4

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 6:1-4 አማ2000

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰዎች በም​ድር ላይ መብ​ዛት በጀ​መሩ ጊዜ መልከ መል​ካ​ሞች ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “መን​ፈሴ በሰው ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ሥጋ ናቸ​ውና፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆ​ናል” አለ። በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 6:1-4-д зориулсан видео