ኦሪት ዘፍጥረት 5
5
የአዳም ትውልድ
(1ዜ.መ. 1፥1-4)
1የሰዎች የትውልድ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ 2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። እነርሱንም በፈጠረበት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው። 3አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም እንደ ምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። 4አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 5አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
6ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖስንም ወለደ፤ 7ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 8ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
9ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ 10ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 11ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
12ቃይናንም መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፤ መላልኤልንም ወለደ፤ 13ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 14ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
15መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ያሬድንም ወለደ፤ 16መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 17መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
18ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖክንም ወለደ፤ 19ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 20ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
21ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ 22ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ ሄኖክም ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 23ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። 24ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ ስላሰኘው አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ሰውሮታልና።
25ማቱሳላም መቶ ሰማንያ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ስድሳ ሰባት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ላሜሕንም ወለደ፤ 26ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስምንት መቶ ሁለት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። 27ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
28ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሰማንያ ስምንት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። 29ስሙንም ከሥራዬ፥ ከእጄ ድካምና እግዚአብሔር ከረገማት ምድር ይህ ያሳርፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። 30ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት#ዕብ. “አምስት መቶ ዘጠና አምስት” ይላል። ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 31ላሜሕም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባት መቶ ሃምሳ ሦስት” ዕብ. “ሰባት መቶ ሰባ ሰባት” ይላል። ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
32ለኖኅም አምስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።
Одоогоор Сонгогдсон:
ኦሪት ዘፍጥረት 5: አማ2000
Тодруулга
Хуваалцах
Хувилах
Тодруулсан зүйлсээ бүх төхөөрөмждөө хадгалмаар байна уу? Бүртгүүлэх эсвэл нэвтэрнэ үү