1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፥ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፥ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
Харьцуулах
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27 г судлах
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28 г судлах
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1 г судлах
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2 г судлах
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3 г судлах
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31 г судлах
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4 г судлах
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29 г судлах
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5 г судлах
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6 г судлах
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30 г судлах
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14 г судлах
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11 г судлах
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7 г судлах
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12 г судлах
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16 г судлах
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10 г судлах
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22 г судлах
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24 г судлах
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20 г судлах
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25 г судлах
Нүүр хуудас
Библи
Тѳлѳвлѳгѳѳнүүд
Бичлэгүүд