1
ዘፍጥረት 9:12-13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋራ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋራ፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Спореди
Истражи ዘፍጥረት 9:12-13
2
ዘፍጥረት 9:16
ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔርና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”
Истражи ዘፍጥረት 9:16
3
ዘፍጥረት 9:6
“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል፣ እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።
Истражи ዘፍጥረት 9:6
4
ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤
Истражи ዘፍጥረት 9:1
5
ዘፍጥረት 9:3
ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
Истражи ዘፍጥረት 9:3
6
ዘፍጥረት 9:2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታትና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
Истражи ዘፍጥረት 9:2
7
ዘፍጥረት 9:7
እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”
Истражи ዘፍጥረት 9:7
Дома
Библија
Планови
Видеа