YouVersion logotips
Meklēt ikonu

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 7

7
ማየ አይኅ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና። 2ከን​ጹሕ እን​ስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆ​ነም እን​ስሳ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት፤ 3ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ። 4ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።” 5ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ። 6ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።
7ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ። 8ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችና ንጹ​ሓን ካል​ሆኑ ወፎች፥ ከን​ጹሕ እን​ስሳ፥ ንጹ​ሕም ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ፥ 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መር​ከብ ውስጥ ገቡ። 10ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ ሆነ። 11በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥#ግዕዙ “አመ 10ወ2 ለጽ​ል​መት” ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት” ይላል። በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤ 12ዝና​ቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ሆነ።
13በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ። 14አራ​ዊ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ወፎ​ችም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ የሚ​በሩ ወፎ​ችም ሁሉ፥ 15ሥጋ ያላ​ቸው ሕያ​ዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ መር​ከብ ውስጥ ገቡ። 16ሥጋ ካለው ሁሉ የገ​ቡ​ትም ተባ​ትና እን​ስት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መር​ከ​ብ​ዋን በስ​ተ​ውጭ ዘጋት። 17የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። 18ውኃ​ውም አሸ​ነፈ፤ በም​ድር ላይም እጅግ በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም በውኃ ላይ ተን​ሳ​ፈ​ፈች። 19ውኃ​ውም በም​ድር ላይ እጅግ በጣም አሸ​ነፈ፤ ከሰ​ማይ በታች ያሉ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ችን ሁሉ ሸፈነ። 20ውኃው ወደ ላይ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ፤ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ች​ንም ሸፈነ። 21በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ። 22የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ፥ በየ​ብ​ስም ያለው ሁሉ ሞተ። 23በም​ድር ላይ የነ​በ​ረ​ውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ፥ እስ​ከ​ሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰ​ውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደ​መ​ሰሰ፤ ከም​ድ​ርም ተደ​መ​ሰሱ። ኖኅም አብ​ረ​ውት በመ​ር​ከብ ከነ​በ​ሩት ጋር ብቻ​ውን ቀረ። 24ውኃ​ውም መቶ አምሳ ቀን በም​ድር ላይ ሞላ።

Izceltais

Dalīties

Kopēt

None

Vai vēlies, lai tevis izceltie teksti tiktu saglabāti visās tavās ierīcēs? Reģistrējieties vai pierakstieties