1
ዮሐንስ 3:16
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።
Salīdzināt
Izpēti ዮሐንስ 3:16
2
ዮሐንስ 3:17
እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።
Izpēti ዮሐንስ 3:17
3
ዮሐንስ 3:3
ኢየሱስም መልሶ፣ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው።
Izpēti ዮሐንስ 3:3
4
ዮሐንስ 3:18
በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።
Izpēti ዮሐንስ 3:18
5
ዮሐንስ 3:19
ፍርዱም ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤
Izpēti ዮሐንስ 3:19
6
ዮሐንስ 3:30
እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል።
Izpēti ዮሐንስ 3:30
7
ዮሐንስ 3:20
ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ አድራጎቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።
Izpēti ዮሐንስ 3:20
8
ዮሐንስ 3:36
በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
Izpēti ዮሐንስ 3:36
9
ዮሐንስ 3:14
ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤
Izpēti ዮሐንስ 3:14
10
ዮሐንስ 3:35
አብ ወልድን ይወድዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።
Izpēti ዮሐንስ 3:35
Mājas
Bībele
Plāni
Video