የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24

24
ጌታ ስለ መነ​ሣቱ
1ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ያዘ​ጋ​ጁ​ትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማል​ደው ወደ መቃ​ብሩ ሄዱ፤ ሌሎች ሴቶ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ። 2ያቺ​ንም ድን​ጋይ ከመ​ቃ​ብሩ ላይ ተን​ከ​ባ​ልላ አገ​ኙ​አት። 3ገብ​ተ​ውም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ አላ​ገ​ኙም። 4ስለ​ዚ​ህም ነገር የሚ​ሉ​ትን አጥ​ተው ሲያ​ደ​ንቁ ሁለት ሰዎች ከፊ​ታ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ነበር። 5ፈር​ተ​ውም ፊታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አቀ​ረ​ቀሩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ሕያ​ዉን ከሙ​ታን ጋር ለምን ትሹ​ታ​ላ​ችሁ? 6በዚህ የለም፤ ተነ​ሥ​ቶ​አል። በገ​ሊላ ሳለ ለእ​ና​ንተ እን​ዲህ ሲል የተ​ና​ገ​ረ​ውን ዐስቡ፦ 7#ማቴ. 16፥21፤ 17፥22-23፤ 20፥18-19፤ ማር. 8፥31፤ 9፥31። የሰው ልጅ በኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ሰዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይሰ​ቅ​ሉ​ታል፤ ይገ​ድ​ሉ​ታል፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ሣል።” 10፥33-34፤ ሉቃ. 9፥22፤ 18፥31-33። 8ቃሉ​ንም ዐሰቡ። 9ከመ​ቃ​ብ​ርም ተመ​ል​ሰው ለዐ​ሥራ አን​ዱና ለቀ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይህን ነገር ነገ​ሩ​አ​ቸው። 10እነ​ዚ​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያም፥ ዮሐና፥ የያ​ዕ​ቆብ እናት ማር​ያም፥ አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ይህን ለሐ​ዋ​ር​ያት ነገ​ሩ​አ​ቸው። 11ይህም ነገር በፊ​ታ​ቸው እንደ ተረት መሰ​ላ​ቸ​ውና አላ​መ​ኑ​አ​ቸ​ውም። 12ጴጥ​ሮ​ስም ተነሣ፤ ወደ መቃ​ብ​ርም ፈጥኖ ሄደ፤ ዝቅ ብሎም በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ በፍ​ታ​ውን ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ አየ፤ የሆ​ነ​ው​ንም እያ​ደ​ነቀ ተመ​ለሰ።
በኤ​ማ​ሁስ መን​ገድ ስላ​ገ​ኙት ሰዎች
13በዚ​ያም ቀን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስድሳ ምዕ​ራፍ ያህል ወደ​ም​ት​ር​ቀው ኤማ​ሁስ ወደ​ም​ት​ባ​ለው መን​ደር ሄዱ። 14እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። 15እነ​ር​ሱም ይህን ሲነ​ጋ​ገ​ሩና ሲመ​ራ​መሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ እነ​ርሱ ቀረበ፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ሄደ። 16እን​ዳ​ያ​ው​ቁ​ትም ዐይ​ና​ቸው ተይዞ ነበር። 17ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። 18ከእ​ነ​ር​ሱም ቀለ​ዮጳ የሚ​ባ​ለው አንዱ መልሶ፥ “አንተ ብቻ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ግዳ ነህን? በእ​ነ​ዚህ ቀኖ​ችስ በው​ስ​ጥዋ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው። 19ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በቃ​ሉና በሥ​ራው ብርቱ ነቢ​ይና እው​ነ​ተኛ ሰው ስለ​ነ​በ​ረው ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ፥ 20የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ል​ፈው እንደ ሰጡት፥ ሞትም እንደ ፈረ​ዱ​በ​ትና እንደ ሰቀ​ሉት ነው። 21እኛ ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ እና​ደ​ርግ ነበር፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ይህ ነገር ከሆነ ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀን ነው። 22ደግ​ሞም ሴቶች ከእኛ ዘንድ ወደ መቃ​ብር ገስ​ግ​ሠው ሄደው ነበ​ርና አስ​ደ​ን​ቀው ነገ​ሩን። 23ሥጋ​ው​ንም በአ​ላ​ገኙ ጊዜ ተመ​ል​ሰው፦ ተነ​ሥ​ቶ​አል ያሉ​አ​ቸ​ውን የመ​ላ​እ​ክ​ትን መልክ እንደ አዩ ነገ​ሩን። 24ከእ​ኛም ዘንድ ወደ መቃ​ብር ሄደው እን​ዲሁ ሴቶች እንደ ተና​ገ​ሩት ሆኖ ያገ​ኙት አሉ፤ እር​ሱን ግን አላ​ዩ​ትም።” 25ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ ነቢ​ያ​ትም የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር ሁሉ ከማ​መን ልባ​ችሁ የዘ​ገየ፥ 26ክር​ስ​ቶስ እን​ዲህ ይሞት ዘንድ ወደ ክብ​ሩም ይመ​ለስ ዘንድ ያለው አይ​ደ​ለ​ምን?” 27እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።
28ሊሄ​ዱ​ባት ወደ ነበ​ረ​ችው መን​ደ​ርም ተቃ​ረቡ፤ እርሱ ግን ይር​ቃ​ቸው ጀመር። 29እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ። 30ከዚ​ህም በኋላ አብ​ሮ​አ​ቸው ለማ​ዕድ ተቀ​ምጦ ሳለ እን​ጀ​ራ​ውን አን​ሥቶ ባረከ፤ ቈር​ሶም ሰጣ​ቸው። 31ዐይ​ና​ቸ​ውም ተገ​ለ​ጠና ዐወ​ቁት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ከእ​ነ​ርሱ ተሰ​ወረ። 32እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”
ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ መመ​ለ​ሳ​ቸው
33በዚ​ያ​ችም ሰዓት ተነ​ሥ​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ዐሥራ አን​ዱን ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ት​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው አገ​ኙ​አ​ቸው፤ 34እን​ዲህ እያሉ፥ “ጌታ​ችን በእ​ው​ነት ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ለስ​ም​ዖ​ንም ታይ​ቶ​ታል።” 35እነ​ር​ሱም በመ​ን​ገድ የሆ​ነ​ው​ንና እን​ጀ​ራ​ውን ሲቈ​ርስ ጌታ​ች​ንን እን​ዴት እን​ዳ​ወ​ቁት ነገ​ሩ​አ​ቸው።
ጌታ​ችን ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ መገ​ለጡ
36ይህ​ንም ሲነ​ጋ​ገሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አት​ፍሩ፤ እኔ ነኝ” አላ​ቸው። 37እነ​ርሱ ግን ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ምት​ሐ​ት​ንም የሚ​ያዩ መሰ​ላ​ቸው። 38እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ኋል? በል​ባ​ች​ሁስ እን​ዲህ ያለ ዐሳብ ለምን ይነ​ሣ​ሣል? 39እጄ​ንና እግ​ሬን እዩ፤ ዳስ​ሱ​ኝም፤ እኔ እንደ ሆን​ሁም ዕወቁ፤ በእኔ እን​ደ​ም​ታ​ዩት ለም​ት​ሐት አጥ​ን​ትና ሥጋ የለ​ው​ምና።” 40ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና እግ​ሮ​ቹን አሳ​ያ​ቸው። 41ከድ​ን​ጋጤ የተ​ነ​ሣም ገና ሳያ​ምኑ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ሲያ​ደ​ንቁ ሳሉ፥ “በዚህ አን​ዳች የሚ​በላ አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። 42እነ​ር​ሱም ከተ​ጠ​በሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፤ ከማር ወለ​ላም ጥቂት ሰጡት። 43ተቀ​ብ​ሎም በፊ​ታ​ቸው በላ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው።#“የተ​ረ​ፈ​ው​ንም አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
44እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው። 45ከዚ​ህም በኋላ መጻ​ሕ​ፍ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ተ​ውሉ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ከፈ​ተ​ላ​ቸው። 46እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ 47ንስ​ሓና የኀ​ጢ​ኣት ስር​የት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጀምሮ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ሰ​በክ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አል። 48እና​ን​ተም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮች ናችሁ። 49#የሐዋ. 1፥4። እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”
ስለ ዕር​ገቱ
50እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው። 51#የሐዋ. 1፥9-11። እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ። 52እነ​ር​ሱም ሰገ​ዱ​ለ​ትና በታ​ላቅ ደስታ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ። 53በቤተ መቅ​ደ​ስም ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ገ​ለ​ገሉ ኖሩ።
ከሰባ ሁለቱ አር​ድ​እት አንዱ ወን​ጌ​ላዊ ሉቃስ የጻ​ፈው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ።
የጻ​ፈ​ውም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ ሰማይ በዐ​ረገ በሃያ አንድ ዓመት ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራት ዓመት በጽ​ርዕ ቋንቋ ለመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ነው።
ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in