ኦሪት ዘፍጥረት 5

5
የአዳም ዘሮች
(1ዜ.መ. 1፥1-4)
1የአዳም የዘር ሐረግ ከዚህ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤ #ዘፍ. 1፥27-28። 2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ “ሰው” ብሎም ሰየማቸው። #ማቴ. 19፥4፤ ማር. 10፥6። 3አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት። 4ከዚህ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 5ዕድሜው 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
6ሴት 105 ዓመት ሲሆነው ሄኖስን ወለደ፤ 7ከዚህ በኋላ ሴት 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 8ዕድሜው 912 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
9ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ፤ 10ከዚህ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 11ዕድሜው 905 ሲሆነውም ሞተ።
12ቃይናንም 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ፤ 13ከዚህ በኋላ 840 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 14ዕድሜው 910 ሲሆነውም ሞተ።
15መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ፤ 16ከዚህ በኋላ 830 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 17ዕድሜው 895 ሲሆነውም ሞተ።
18ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሔኖክን ወለደ፤ 19ከዚህ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 20ዕድሜው 962 ሲሆነውም ሞተ።
21ሔኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ፤ 22ከዚህ በኋላ ሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 23ዕድሜው 365 እስኪሆነው ድረስ ኖረ፤ 24ይህን ያኽል ዘመን የኖረውም የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ነበር፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ወሰደው አልተገኘም። #ዕብ. 11፥5፤ ይሁዳ 14።
25ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜክን ወለደ፤ 26ከዚህ በኋላ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 27ዕድሜው 969 ሲሆነውም ሞተ።
28ላሜክ 182 ዓመት ሲሆነው ወንድ ልጅ ወለደ፤ 29“ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ላይ ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። #5፥29 ኖኅ፦ በዕብራይስጥ “ዕረፍት” ማለት ነው። 30ከዚህ በኋላ ላሜክ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 31ዕድሜው 777 ሲሆነውም ሞተ።
32ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ይባሉ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in