የሉ​ቃስ ወን​ጌል 8

8
ጌታ​ችን የገ​ሊ​ላን አው​ራ​ጃ​ዎች ተዘ​ዋ​ውሮ ስለ ማስ​ተ​ማሩ
1ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በየ​ከ​ተ​ማ​ዉና በየ​መ​ን​ደሩ ተመ​ላ​ለሰ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ግ​ሥት ሰበ​ከ​ላ​ቸው፤ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። 2ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትና ከደ​ዌ​ያ​ቸው ያዳ​ና​ቸው ሴቶ​ችም አብ​ረ​ውት ነበሩ። እነ​ር​ሱም፦ መግ​ደ​ላ​ዊት የም​ት​ባ​ለው ሰባት አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ላት ማር​ያም፥ 3#ማቴ. 27፥55-56፤ ማር. 15፥40-44፤ ሉቃ. 23፥49። የሄ​ሮ​ድስ አዛዥ የነ​በ​ረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስ​ናም፥ በገ​ን​ዘ​ባ​ቸው ያገ​ለ​ግ​ሉት#በግ​ሪኩ “ያገ​ለ​ግ​ሏ​ቸው” ነበር ይላል። የነ​በሩ ብዙ​ዎች ሌሎ​ችም ነበሩ።
ስለ ዘሪው ምሳሌ
4ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ ከየ​ከ​ተ​ማ​ዉም ሁሉ ወደ እርሱ የመ​ጡት ሲያ​ዳ​ም​ጡት እን​ዲህ ያለ ምሳሌ ነገ​ራ​ቸው። 5“ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ፤ ሲዘ​ራም አን​ዳ​ንዱ በመ​ን​ገድ ወደ​ቀና ተረ​ገጠ፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም በሉት። 6ሌላ​ውም በጭ​ንጫ መሬት ላይ ወደቀ፤ በበ​ቀ​ለም ጊዜ ወዲ​ያው ደረቀ፤ ሥር አል​ነ​በ​ረ​ው​ምና። 7ሌላ​ዉም በእ​ሾህ መካ​ከል ወደቀ፤ እሾ​ሁም አብሮ አደ​ገና አነ​ቀው። 8በመ​ል​ካም መሬት ላይ የወ​ደቀ ዘርም ነበረ፤ በበ​ቀ​ለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ።” ይህ​ንም ብሎ፥ “የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አላ​ቸው።
9ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “ይህቺ ምሳሌ ምን​ድን ናት?” ብለው ጠየ​ቁት። 10#ኢሳ. 6፥9-10። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው። 11ምሳ​ሌ​ዉም ይህ ነው፤ ዘሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤ 12በመ​ን​ገድ የወ​ደ​ቀው ቃሉን የሚ​ሰሙ ናቸው፤ አም​ነ​ውም እን​ዳ​ይ​ድኑ ሰይ​ጣን መጥቶ ቃሉን ከል​ባ​ቸው ይወ​ስ​ድ​ባ​ቸ​ዋል። 13በጭ​ን​ጫም ላይ የወ​ደ​ቀው ሰም​ተው ነገ​ሩን በደ​ስታ የሚ​ቀ​በ​ሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊ​ዜው ያም​ናሉ እንጂ ሥር የላ​ቸ​ውም፤ መከ​ራም በአ​ገ​ኛ​ቸው ጊዜ ይክ​ዳሉ። 14በእ​ሾ​ህም መካ​ከል የወ​ደ​ቀው ቃሉን ሰም​ተው የባ​ለ​ጠ​ግ​ነት ዐሳብ፥ የኑ​ሮም መቈ​ር​ቈር የተ​ድ​ላና የደ​ስታ መጣ​ፈ​ጥም የሚ​አ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ውና ፍሬ የማ​ያ​ፈሩ ናቸው። 15በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።
16 # ማቴ. 5፥15፤ ሉቃ. 11፥33። “መብ​ራ​ትን አብ​ርቶ፥ ዕቃም ከድኖ ከአ​ልጋ በታች የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም፤ ነገር ግን የሚ​መ​ላ​ለ​ሱት ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረዝ ላይ ያኖ​ራ​ታል። 17#ማቴ. 10፥26፤ ሉቃ. 12፥2። የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ የለ​ምና፤ የማ​ይ​ታ​ይም ወደ ግል​ጥም የማ​ይ​መጣ የተ​ከ​ደነ የለም፤ 18#ማቴ. 25፥29፤ ሉቃ. 19፥26። እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሰሙ አስ​ተ​ውሉ፤ ላለው ይሰ​ጠ​ዋል፤ ከሌ​ለው ግን ያው ያለው የሚ​መ​ስ​ለው እንኳ ይወ​ሰ​ድ​በ​ታል።”
ወን​ድ​ሞቹ ስለ​ሚ​ባ​ሉት የተ​ና​ገ​ረው
19እና​ቱና ወን​ድ​ሞ​ቹም ወደ እርሱ መጡ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነበ​ርና ሊያ​ገ​ኙት አል​ቻ​ሉም። 20“እና​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ ከውጭ ቆመ​ዋል፤ ሊያ​ዩ​ህም ይሻሉ” አሉት። 21እር​ሱም መልሶ፥ “እና​ቴና ወን​ድ​ሞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ያ​ደ​ርጉ እነ​ዚህ ናቸው” አላ​ቸው።
ባሕ​ርን ስለ መገ​ሠጹ
22ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ። 23ሲሄ​ዱም አን​ቀ​ላፋ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃ​ዉም ታን​ኳ​ቸ​ውን ሞላው፤ እነ​ር​ሱም ተጨ​ነቁ። 24ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ። 25እር​ሱም “እም​ነ​ታ​ችሁ ወዴት አለ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ፈር​ተው ተደ​ነቁ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ውኃም ነፋ​ስም የሚ​ታ​ዘ​ዙ​ለት ይህ ማነው?” አሉ።
ጋኔን ያደ​ረ​በ​ትን ሰው ስለ ማዳኑ
26ከዚህ በኋላ በገ​ሊላ ወደብ አቅ​ጣጫ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ኖን ሀገር በታ​ንኳ ሄዱ። 27ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ጋኔን ያደ​ረ​በት ሰው ከከ​ተማ ወጥቶ ተገ​ና​ኘው፤ ልብ​ሱ​ንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመ​ቃ​ብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይ​ገ​ባም ነበር፤ 28ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው። 29ክፉ​ውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እን​ዲ​ወጣ ያዝ​ዘው ነበ​ርና፤ ዘወ​ት​ርም አእ​ም​ሮ​ዉን ያሳ​ጣው ነበ​ርና፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በእ​ግር ብረት አስ​ረው ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ እግር ብረ​ቱ​ንም ይሰ​ብር ነበር፤ ጋኔ​ኑም በም​ድረ በዳ ያዞ​ረው ነበር። 30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስምህ ማነው?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ስሜ ሌጌ​ዎን ነው” አለው፤ ብዙ አጋ​ን​ንት ይዘ​ውት ነበ​ርና። 31ወደ ጥል​ቁም ይገቡ ዘንድ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ዳ​ቸው ማለ​ዱት። 32በዚ​ያም ብዙ የእ​ሪያ መንጋ በተ​ራራ ላይ ተሰ​ማ​ርቶ ነበር፤ ወደ እሪ​ያ​ዎ​ችም እን​ዲ​ገ​ቡ​ባ​ቸው ይፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ማለ​ዱት፤ እር​ሱም ፈቀ​ደ​ላ​ቸው። 33እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።
34እረ​ኞ​ችም የሆ​ነ​ውን ባዩ ጊዜ ሸሽ​ተው ሄዱና ገብ​ተው በከ​ተ​ማ​ዉና በመ​ን​ደሩ አወሩ። 35ሰዎ​ችም የሆ​ነ​ውን ያዩ ዘንድ ወጡ፤ ሄደ​ውም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ በደ​ረሱ ጊዜ አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለ​ትን ያን ሰው አእ​ም​ሮዉ ተመ​ል​ሶ​ለት ልብ​ሱን ለብሶ፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ አገ​ኙ​ትና ፈሩ። 36ያዩ​ትም ሰዎች ጋኔን አድ​ሮ​በት የነ​በ​ረው ሰው እን​ዴት እንደ ዳነ ነገ​ሩ​አ​ቸው። 37በጌ​ር​ጌ​ሴ​ኖ​ንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ሄ​ድ​ላ​ቸው ማለ​ዱት፤ ጽኑ ፍር​ሀት ይዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በታ​ንኳ ሆኖ ተመ​ለሰ። 38ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤ 39እርሱ ግን፥ “ወደ ቤትህ ተመ​ል​ሰህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ል​ህን ታላቅ ነገር ሁሉ ተና​ገር” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው። እር​ሱም ሄዶ በከ​ተ​ማዉ ሁሉ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ሁሉ ተና​ገረ። 40ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ሕዝቡ በአ​ን​ድ​ነት ተቀ​በ​ሉት፤ ሁሉ ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበ​ርና።
ስለ ምኵ​ራቡ ሹም ልጅና ደም ይፈ​ስ​ስ​ባት ስለ ነበ​ረ​ችው ሴት
41እነ​ሆም ኢያ​ኢ​ሮስ የሚ​ባል ሰው መጣ፤ እር​ሱም የም​ኵ​ራብ ሹም ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር በታ​ችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመ​ነው። 42ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።
43ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም። 44ቀር​ባም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆመ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ ዳሰ​ሰች፤ ያን​ጊ​ዜም የደ​ምዋ መፍ​ሰስ ቆመ። 45ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማን ዳሰ​ሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሰው ይጋ​ፋ​ህና ያጨ​ና​ን​ቅህ የለ​ምን? አንተ ግን ማን ዳሰ​ሰኝ? ትላ​ለህ” አሉት። 46ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የዳ​ሰ​ሰኝ አለ፤ ከእኔ ኀይል እንደ ወጣ ዐው​ቃ​ለ​ሁና” አላ​ቸው። 47ሴቲ​ቱም እን​ዳ​ል​ተ​ሰ​ወ​ረ​ላት ባየች ጊዜ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ሄዳ ሰገ​ደ​ች​ለት፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በምን ምክ​ን​ያት ወደ እርሱ እንደ ቀረ​በ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ እንደ ዳሰ​ሰች ወዲ​ያ​ውም እንደ ዳነች ተና​ገ​ረች። 48እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እም​ነ​ትሽ አዳ​ነ​ችሽ፤ በሰ​ላም ሂጂ” አላት። 49ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው። 50ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በሰማ ጊዜ የም​ኵ​ራ​ቡን ሹም፥ “አት​ፍራ፥ ብቻ እመን፤ ልጅ​ህስ ትድ​ና​ለች” አለው። 51ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴ​ጥ​ሮስ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብና ከዮ​ሐ​ንስ፥ ከብ​ላ​ቴ​ና​ይ​ቱም አባ​ትና እናት በቀር ማንም ከእ​ርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም። 52ሁሉም እያ​ለ​ቀሱ ዋይ ዋይ ይሉ​ላት ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን፥ “አታ​ል​ቅሱ፤ ብላ​ቴ​ና​ይቱ ተኝ​ታ​ለች እንጂ አል​ሞ​ተ​ችም” አላ​ቸው። 53እንደ ሞተ​ችም ዐው​ቀ​ዋ​ልና ሳቁ​በት። 54እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስ​ወ​ጣና እጅ​ዋን ይዞ ጠራት፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “ አንቺ ብላ​ቴና ተነሺ።” 55ወዲ​ያ​ውም ነፍ​ስዋ ተመ​ል​ሶ​ላት ፈጥና ቆመች፥ የም​ት​በ​ላ​ው​ንም ይሰ​ጡ​አት ዘንድ አዘዘ። 56አባ​ቷና እና​ቷም አደ​ነቁ፤ እርሱ ግን የሆ​ነ​ውን ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሩ ከለ​ከ​ላ​ቸው።

ハイライト

シェア

コピー

None

すべてのデバイスで、ハイライト箇所を保存したいですか? サインアップまたはサインインしてください。