1
ኦሪት ዘፍጥረት 11:6-7
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ጌታም አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ ሕዝቦች አንድ ወገን ናቸው፥ የሁሉም መነጋገሪያ ቋንቋም አንድ ነው። አሁን ይህን ማድረግ ጀመሩ፥ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ስለዚህ ኑ! እንውረድ፥ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”
比較
ኦሪት ዘፍጥረት 11:6-7で検索
2
ኦሪት ዘፍጥረት 11:4
እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።
ኦሪት ዘፍጥረት 11:4で検索
3
ኦሪት ዘፍጥረት 11:9
ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 11:9で検索
4
ኦሪት ዘፍጥረት 11:1
በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩበትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 11:1で検索
5
ኦሪት ዘፍጥረት 11:5
ጌታም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
ኦሪት ዘፍጥረት 11:5で検索
6
ኦሪት ዘፍጥረት 11:8
ከዚያ በኋላ ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፥ ከተማይቱንም መሥራት አቆሙ።
ኦሪት ዘፍጥረት 11:8で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ