1
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በእርሳችሁ ከተዋደዳችሁ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰው ሁሉ ያውቃል።”
比較
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35で検索
2
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15
እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁት እናንተም እንድታደርጉ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15で検索
3
የዮሐንስ ወንጌል 13:7
ኢየሱስም “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 13:7で検索
4
የዮሐንስ ወንጌል 13:16
እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላኪው አይበልጥም።
የዮሐንስ ወንጌል 13:16で検索
5
የዮሐንስ ወንጌል 13:17
ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:17で検索
6
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5
ስለዚህ ከማእድ ተነሣና ልብሱን አስቀመጠ፤ ማበሻ ጨርቅም አንሥቶ በወገቡ ታጠቀ። ከዚህ በኋላ በመታጠቢያ ዕቃ ውሃ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብ ጀመረ፤ በታጠቀውም ማበሻ ጨርቅ እግራቸውን አበሰ።
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ