1
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ጋር ለምገባው ለዚህ ለዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ፥ ቀስቴን በደመናዎች ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም ቀስት ከምድር ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ይኖራል።
比較
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13で検索
2
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16で検索
3
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6で検索
4
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ፥ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1で検索
5
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
ከዚህ በፊት የአትክልት ዐይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3で検索
6
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2で検索
7
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
“እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ