1
ኦሪት ዘፍጥረት 3:6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
比較
ኦሪት ዘፍጥረት 3:6で検索
2
ኦሪት ዘፍጥረት 3:1
እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:1で検索
3
ኦሪት ዘፍጥረት 3:15
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 3:15で検索
4
ኦሪት ዘፍጥረት 3:16
ሴቲቱንም፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቀትሽን፥ በምትወልጂበትም ጊዜ የምጥ ሥቃይሽን አበዛሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል። ለእርሱም ታዛዥ ትሆኚአለሽ” አላት።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:16で検索
5
ኦሪት ዘፍጥረት 3:19
ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:19で検索
6
ኦሪት ዘፍጥረት 3:17
አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:17で検索
7
ኦሪት ዘፍጥረት 3:11
እግዚአብሔርም “እራቁትህን እንደ ሆንክ ማን ነገረህ? አትብላ ካልኩህ ዛፍ ፍሬ ወስደህ በላህን?” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:11で検索
8
ኦሪት ዘፍጥረት 3:24
አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:24で検索
9
ኦሪት ዘፍጥረት 3:20
አዳምም ሚስቱ ሕይወት ላላቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ሁሉ እናት ስለ ሆነች “ሔዋን” የሚል ስም አወጣላት።
ኦሪት ዘፍጥረት 3:20で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ