1
የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስም “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በሕይወት የሚኖርና በእኔም የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽ?” አላት።
Bera saman
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:25-26
2
የዮሐንስ ወንጌል 11:40
ኢየሱስም “ካመንሽ የእግዚአብሔርን ክብር ታያለሽ ብዬሽ አልነበረምን?” አላት።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:40
3
የዮሐንስ ወንጌል 11:35
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:35
4
የዮሐንስ ወንጌል 11:4
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:4
5
የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ “አልዓዛር! ና ውጣ!” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተናገረ። ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:43-44
6
የዮሐንስ ወንጌል 11:38
ኢየሱስ በጣም እያዘነ ወደ መቃብሩ ሄደ፤ መቃብሩ በድንጋይ የተዘጋ ዋሻ ነበር።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:38
7
የዮሐንስ ወንጌል 11:11
ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፤ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አለ።
Njòttu የዮሐንስ ወንጌል 11:11
Heim
Biblía
Áætlanir
Myndbönd