1
የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፥ በሙሉ ነፍስህ፥ በሙሉ ሐሳብህ ውደድ፤ ከሁሉ የሚበልጠውና የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው። ይህንንም የሚመስለው ሁለተኛው ትእዛዝ፥ ‘ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤’ የሚለው ነው።
Compare
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
2
የማቴዎስ ወንጌል 22:40
የሕግና የነቢያት ትምህርት ሁሉ የተመሠረቱት በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዞች ላይ ነው።”
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:40
3
የማቴዎስ ወንጌል 22:14
ቀጥሎም ኢየሱስ “ስለዚህ የተጠሩ ብዙዎች ናቸው፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው” አለ።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:14
4
የማቴዎስ ወንጌል 22:30
በሙታን ትንሣኤ ጊዜ ሰዎች በሰማይ እንዳሉት መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:30
5
የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስቲ አሳዩኝ!” አላቸው። ስለዚህ እነርሱ አንድ ዲናር አምጥተው አሳዩት። እርሱም፥ “በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም፥ “የሮማው ንጉሠ ነገሥት ነው!” አሉት፤ እርሱም፥ “እንግዲያውስ የንጉሡን ለንጉሡ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤” አላቸው።
Explore የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
Home
Bible
Plans
Videos