1
የዮሐንስ ወንጌል 6:35
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ለዘለዓለም አይጠማም።
Sammenlign
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:35
2
የዮሐንስ ወንጌል 6:63
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አንዳች አይጠቅምም፤ ይህም እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:63
3
የዮሐንስ ወንጌል 6:27
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:27
4
የዮሐንስ ወንጌል 6:40
የአባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወልድን አይቶ የሚያምንበት ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።”
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:40
5
የዮሐንስ ወንጌል 6:29
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ ነው፤” አላቸው።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:29
6
የዮሐንስ ወንጌል 6:37
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:37
7
የዮሐንስ ወንጌል 6:68
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ ማን እንሄዳለን?
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:68
8
የዮሐንስ ወንጌል 6:51
“ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው ይህ እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:51
9
የዮሐንስ ወንጌል 6:44
የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣትን የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:44
10
የዮሐንስ ወንጌል 6:33
የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ፤ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና።”
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:33
11
የዮሐንስ ወንጌል 6:48
የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:48
12
የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
ጌታችን ኢየሱስም ያን እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ ከዓሣውም እንዲሁ የፈለጉትን ያህል ሰጡአቸው። ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ከቍርስራሹ ምንም የሚወድቅ እንዳይኖር የተረፈውን ቍርስራሽ አንሡ፤” አላቸው።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:11-12
13
የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስን በባሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታንኳዉ በቀረበ ጊዜም ፈሩ። እርሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።
Udforsk የዮሐንስ ወንጌል 6:19-20
Hjem
Bibel
Læseplaner
Videoer