የሉቃስ ወንጌል 19
19
ኢየሱስ እና ቀራጩ ዘኬዎስ
1ወደ ኢያሪኮም ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። 2እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው ነበረ፤ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፤ ሀብታምም ነበረ። 3ኢየሱስ ማን እንደሆነም ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አቃተው። 4በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። 5ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና “ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በቤትህ መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ፤” አለው። 6ፈጥኖም ወረደ፤ በደስታም ተቀበለው። 7ሁሉም አይተው “ከኀጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ፤” ብለው አንጐራጐሩ። 8ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ! ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ፤” አለው። 9ኢየሱስም “ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን መጥቶ አል፤ ምክንያቱም እርሱም የአብርሃም ልጅ ነውና፤ 10#ማቴ. 18፥11።የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና፤” አለው።
የዐሥሩ ምናን ምሳሌ
(ማቴ. 25፥14-30)
11እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሳለ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡ፥ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ እንደሚገለጥ ይገምቱ ነበርና፥ ተጨማሪ ምሳሌ ነገራቸው። 12እንዲህም አላቸው “አንድ መኰንን ለራሱ የመንግሥትን ሥልጣን ተቀብሎ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። 13ዐሥር አገልጋዮችንም ጠርቶ ዐሥር ምናን#19፥13 የግሪካውያን የገንዘብ መለኪያ። ሰጣቸውና ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱ፤’ አላቸው። 14የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና ‘ይህ በላያችን እንዲነግሥ አንፈልግም፤’ ብለው በኋላው መልእክተኞችን ላኩ። 15መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ለማወቅ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን አግልጋዮች እንዲጠሩለት አዘዘ። 16የመጀመሪያውም ደርሶ ‘ጌታ ሆይ! ምናንህ ዐሥር ምናን አተረፈ፤’ አለው። 17እርሱም ‘መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ፥ በጥቂት ነገር የታመንህ ስለ ሆንክ በዐሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ፤’ አለው። 18ሁለተኛውም መጥቶ ‘ጌታ ሆይ! ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ፤’ አለው። 19ይህናውንም ‘አንተንም በአምስት ከተማዎች ላይ ሾሜሃለው፤’ አለው። 20ሌላውኛውም መጥቶ ‘ጌታ ሆይ! በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ 21ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንክ፤ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፤ ያልዘራኸውንም የምታጭድ ነህና፤’ አለው። 22እርሱም ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንሁ አወቅህ፤ 23ታዲያ ገንዘቤን ለገንዘብ ለዋጮች#19፥23 ለባንክ። አደራ ያልሰጠኸው ለምንድን ነው? እኔም መጥቼ ከነትርፉ እወስደው ነበር፤’ አለው። 24በዚያም ቆመው የነበሩትን ‘ምናኑን ውሰዱበት፤ ዐሥር ምናን ላለውም ስጡት፤’ አላቸው። 25እነርሱም ‘ጌታ ሆይ! ዐሥር ምናን አለው፤’ አሉት። 26#ማቴ. 13፥12፤ ማር. 4፥25፤ ሉቃ. 8፥18።‘ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ። 27#ማቴ. 25፥14-30።ነገር ግን እነዚያን በላያቸው እንድነግሥ ያልፈለጉትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው፤ በፊቴም እረዱአቸው።’”
ኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ገባ
(ማቴ. 21፥1-11፤ ማር. 11፥1-11፤ ዮሐ. 14፥12-19)
28ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር። 29ደብረዘይት በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበም ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ፤ 30እንዲህም አላቸው፦ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ ወደ እርሷም ገብታችሁ ገና ማንም ሰው ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡት። 31ማንም ‘ስለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉ”። 32የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው ሆኖ አገኙት። 33እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ “ውርንጫውን ስለምን ትፈቱታላችሁ?” አሉአቸው። 34እነርሱም “ለጌታ ያስፈልገዋል፥” አሉ። 35ወደ ኢየሱስም አመጡት፤ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ወርውረው ኢየሱስን አስቀመጡት። 36ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። 37ወደ ደብረዘይት ቁልቁለትም ወዲያው በቀረበ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ በሙሉ ስላዩአቸው ተአምራት ደስ እያላቸው በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ፤ 38#መዝ. 118፥26።እንዲህም አሉ፦ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር፥” አሉ። 39ከሕዝቡም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው፤” አሉት። 40ሲመልስም “እነዚህ እንኳ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ፤እላችኋለሁ” አላቸው።
ኢየሱስ ለኢየሩሳሌም ከተማ ማልቀሱ
41ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤ 42“አንቺስ ለሰላምሽ የሚሆነውን ምነው በዚህ ቀን ባወቅሽ ኖሮ! ነገር ግን አሁን ከዐይንሽ ተሰውሮአል። 43ጠላቶችሽም በዙርያሽ ቅጥር የሚሠሩበት፥ አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁብት ቀኖች ይመጣሉ። 44አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”
ኢየሱስ በቤተ መቅደስ የሚገበያዩትን ሰዎች እንደ አስወጣ
(ማቴ. 21፥12-17፤ ማር. 11፥15-19፤ ዮሐ. 2፥13-22)
45ወደ መቅደስም ገብቶ የሚገበያዩትን ማስወጣት ጀመረ፤ 46#ኢሳ. 56፥7፤ ኤር. 7፥11።እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል፤’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት፤” አላቸው።
47 #
ሉቃ. 21፥37። በየዕለቱም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ መሪዎችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፤ 48የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ በታላቅ ትኩረት ይሰሙት ነበርና።
Dewis Presennol:
የሉቃስ ወንጌል 19: መቅካእኤ
Uwcholeuo
Rhanna
Copi
Eisiau i'th uchafbwyntiau gael eu cadw ar draws dy holl ddyfeisiau? Cofrestra neu mewngofnoda