1
የሐዋርያት ሥራ 5:29
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
Porovnat
Zkoumat የሐዋርያት ሥራ 5:29
2
የሐዋርያት ሥራ 5:42
ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
Zkoumat የሐዋርያት ሥራ 5:42
3
የሐዋርያት ሥራ 5:3-5
ጴጥሮስም፦ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ? ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም” አለው። ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።
Zkoumat የሐዋርያት ሥራ 5:3-5
4
የሐዋርያት ሥራ 5:38-39
አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።”
Zkoumat የሐዋርያት ሥራ 5:38-39
Domů
Bible
Plány
Videa