1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።
Porovnat
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
እኔም አብን እለምናለሁ፤ ለዘለዓለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
አብ በወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:15
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበርን?
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄም ስፍራ ሳዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ዳግምኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም “ጌታ ሆይ! ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው።
Zkoumat የዮሐንስ ወንጌል 14:5
Domů
Bible
Plány
Videa