YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቲቶ 3

3
1-2ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው። 3እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝንት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። 4ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ 5እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ 6-7ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው። 8ቃሉ የታመነ ነው።
እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤ 9ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤ 10-11መለያየትና የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።
12አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቍኦርጬአለሁና። 13ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ። 14ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።
15ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በእምነት ለሚወዱን ሰላምታ አቅርብልን።
ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

Currently Selected:

ወደ ቲቶ 3: አማ54

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in