YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 3

3
ስለ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት ጥያቄ
1እን​ግ​ዲህ አይ​ሁ​ዳዊ የመ​ባል ትርፉ ምን​ድን ነው? የግ​ዝ​ረ​ትስ ጥቅ​ምዋ ምን​ድን ነው? 2በሁሉ ነገር ብዙ ነው፤ ነገር ግን ከዚያ አስ​ቀ​ድሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አደራ ተሰ​ጣ​ቸው። 3የማ​ያ​ምኑ ቢኖ​ሩስ የእ​ነ​ርሱ አለ​ማ​መን ሌላ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ምን ይከ​ለ​ክ​ላ​ልን? አይ​ከ​ለ​ክ​ልም። 4#መዝ. 50፥4። መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና። 5በእኔ ኀጢ​አት#ግሪኩ በእና ኀጢ​አት ...” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከጸና እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰው ላይ ቅጣ​ትን ቢያ​መጣ ይበ​ድ​ላ​ልን? አይ​በ​ድ​ልም፤ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም በሰው ልማድ እና​ገ​ራ​ለሁ። 6እን​ዲ​ህማ ከሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም እን​ደ​ምን ይፈ​ር​ዳል? 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነት በእኔ ሐሰ​ተ​ና​ነት ለክ​ብሩ ከፍ ከአለ እን​ግ​ዲህ እኔን እንደ ኀጢ​አ​ተና ለምን ይፈ​ር​ድ​ብ​ናል? 8በውኑ እና መል​ካም ነገር እና​ገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እና​ድ​ርግ እን​ደ​ም​ንል አስ​መ​ስ​ለው የሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩ​ንና የሚ​ነ​ቅ​ፉን ሰዎች እን​ደ​ሚ​ሰ​ድ​ቡን ነን? ለእ​ነ​ር​ሱስ ቅጣ​ታ​ቸው ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋል።
9እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና። 10መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም። 11አስ​ተ​ዋ​ይም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ሻው የለም። 12#መዝ. 13፥1-3፤ 52፥1-3። ሁሉም ተባ​ብሮ በደለ፤ በጎ ሥራ​ንም የሚ​ሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። 13#መዝ. 5፥9፤ 139፥3። ጕረ​ሮ​አ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ሸነ​ገሉ፤ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤ 14#መዝ. 10፥7። አፋ​ቸው መራራ ነው፤ መር​ገ​ም​ንም የተ​ሞላ ነው። 15እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ደምን ለማ​ፍ​ሰስ ፈጣ​ኖች ናቸው። 16በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ጥፋ​ትና ጕስ​ቍ​ልና አለ። 17#ኢሳ. 59፥7-8። የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቋ​ትም። 18#መዝ. 35፥1። በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት የለም።”
19አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን። 20#መዝ. 142፥2፤ ገላ. 2፥16። ከኦ​ሪት የተ​ነሣ ኀጢ​አት ስለ ታወ​ቀች ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሥር​ዐት በመ​ፈ​ጸም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይ​ጸ​ድ​ቅም።
21አሁን ግን በኦ​ሪ​ትና በነ​ቢ​ያት የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገ​ለ​ጠች። 22#ገላ. 2፥16። የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ድ​ቃሉ። 23በዚ​ህም ልዩ​ነት የለም፤ ሁሉም ፈጽ​መው በድ​ለ​ዋ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማክ​በ​ር​ንም ትተ​ዋ​ልና። 24ጽድቅ ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ቤዛ​ነት ያለ ዋጋ በእ​ርሱ ቸር​ነት ሆነ። 25እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው። 26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጋሽ በመ​ሆኑ፥ እሺ በማ​ለ​ቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው። 27ትም​ክ​ሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀር​ቶ​አል፤ በየ​ት​ና​ውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ሕግ ነው እንጂ። 28ሰው የኦ​ሪ​ትን ሥራ ሳይ​ሠራ በእ​ም​ነት እን​ዲ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና። 29በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ይ​ሁድ ለብ​ቻ​ቸው ነውን? ለአ​ሕ​ዛ​ብስ አይ​ደ​ለ​ምን? 30#ዘዳ. 26፥4፤ ገላ. 3፥20። አዎን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነው፤ የተ​ገ​ዘ​ረ​ውን በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረ​ው​ንም በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው እርሱ አንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። 31እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ኦሪ​ትን እን​ሽ​ራ​ለን? አን​ሽ​ርም፤ ኦሪ​ትን እና​ጸ​ና​ለን እንጂ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in