መዝሙረ ዳዊት 83
83
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1የኀያላን አምላክ ሆይ፥
ማደሪያዎችህ እጅግ የተወደዱ ናቸው።
2አቤቱ፥ ነፍሴ አደባባዮችህን በመውደድ ደስ አላት፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትናፍቃለች” ይላል።
ልቤም ሥጋዬም በሕያው እግዚአብሔር ደስ አላቸው።
3ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥
ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፤
የኀያላን አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥
እርሱ መሠዊያህ ነው።
4በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ብፁዓን ናቸው፤
ለዓለምና ለዘለዓለም ያመስግኑሃል።
5አቤቱ፥ ርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥
በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው።
6በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰንኻቸው ስፍራ
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።#ከዕብራይስጥ ይለያል።
7ከኀይል ወደ ኀይልም ይሄዳል፥#ዕብ. “ይሄዳሉ” ይላል።
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።#ዕብ. “በእግዚአብሔር ፊት” ይላል።
8የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጠኝ።
9አቤቱ፥ መታመኔን እይልኝ፥
ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።
10ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤
በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥
በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።
11እግዚአብሔር አምላክ ምጽዋትንና#ዕብ. “ፀሐይና ጋሻ ነውና” ይላል። እውነትን ይወድዳልና፥
እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን
ከበረከቱ አያሳጣቸውም።
12አቤቱ የኀያላን አምላክ ሆይ፥
በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 83: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in