YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 79

79
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በመ​ለ​ከ​ቶች ስለ አሦ​ራ​ው​ያን የአ​ሳፍ የም​ስ​ክር መዝ​ሙር።
1ዮሴ​ፍን እንደ መንጋ የም​ት​መራ፥#ግእዙ “ዘይ​ር​ዕ​ዮሙ ከመ አባ​ግዐ ዮሴፍ” ይላል።
የእ​ስ​ራ​ኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድ​ምጥ፤
በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ፥ ተገ​ለጥ።
2በኤ​ፍ​ሬ​ምና በብ​ን​ያም በም​ና​ሴም ፊት
ኀይ​ል​ህን አንሣ፥ እኛ​ንም ለማ​ዳን ና።
3የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥#ዕብ. “አም​ላክ ሆይ” ይላል። መል​ሰን፥
ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።
4የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥
በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?
5የእ​ን​ባ​ች​ንን እን​ጀራ ትመ​ግ​በ​ና​ለህ፥
እን​ባ​ች​ን​ንም በስ​ፍር ታጠ​ጣ​ና​ለህ።
6ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን መነ​ጋ​ገ​ሪያ አደ​ረ​ግ​ኸን፥
ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም በላ​ያ​ችን ተሳ​ለ​ቁ​ብን።
7የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ መል​ሰን፥
ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።
8ከግ​ብፅ የወ​ይ​ንን ግንድ አመ​ጣህ፤
አሕ​ዛ​ብን አባ​ረ​ርህ፥ እር​ስ​ዋ​ንም ተከ​ልህ።
9በፊ​ቷም መን​ገ​ድን#ዕብ. “ስፍ​ራን አዘ​ጋ​ጀህ” ይላል። ጠረ​ግህ፥
ሥሮ​ች​ዋ​ንም ተከ​ልህ፥ ምድ​ር​ንም ሞላች።
10ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥
ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።
11ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋ​ንም እስከ ባሕር፥
ቡቃ​ያ​ዋ​ንም እስከ ወንዙ ዘረ​ጋች።
12አጥ​ር​ዋን ለምን አፈ​ረ​ስህ?
መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ይበ​ላ​ታል።
13የበ​ረሃ እርያ አረ​ከ​ሳት፥
የዱር አው​ሬም ተሰ​ማ​ራ​ባት።
14የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ እባ​ክህ ተመ​ለስ፤
ከሰ​ማይ ተመ​ል​ከት፥ እይም፥
ይህ​ች​ንም የወ​ይን ግንድ ይቅር በላት።
15በሰው ልጅ ለአ​ንተ ያጸ​ና​ኻ​ትን
ቀኝህ የተ​ከ​ላ​ትን አጽ​ን​ተህ አነ​ሣ​ሣት።
16በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ላ​ለች፥ ተነ​ቅ​ላ​ማ​ለች
ከፊ​ትህ ተግ​ሣ​ጽም የተ​ነሣ ይጠ​ፋሉ።
17ለአ​ንተ ባጸ​ና​ኸው በሰው ልጅ ላይ፥
በቀ​ኝህ ሰው ላይ እጅህ ይሁን።
18ከአ​ን​ተም አን​ራቅ፤
አድ​ነን፥ ስም​ህ​ንም እን​ጠ​ራ​ለን።
19የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ መል​ሰን፥
ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝ​ሙረ ዳዊት 79